ተናዳፊዋ ንብ
ነፃነት ከልካይ
ነፃነት ከልካይ

አንድ ክፉ ንብ ነበረች ።ከእለታት አንድ ቀን ብዙ ማር አስቀምጣ አበባ ልትቀስም ወደ አበቦቹ ሄደች። በገጠር የሚኖሩ ሁለት ጓደኛሞች አንዱ በረከት ሌላኛው ያሬድ ይባሉ ነበር።

1

እነሱም ሲያልፉ ያስቀመጠችውን ማር አዩባት ፤ ነገርግን በረከት እና ያሬድ ምን እንደሆነ አላወቁም ነበር።በረከትም ይኼ ነገር ማር ነዉ አለዉና ጠጋ ብለዉ አዩት እና ማር እደሆነ አረጋገጡ።

2

ያሬድም በቃ ወደ ቤት እንሂድ እና ለማዉረድ የሚያስፈልገንን ነገር ይዘን እንመለስ አለዉ፡፡ ከዚያም እሺ ተባብለዉ ወደ ቤት ሄደዉ የማር ማድረጊያ ባሊ እና ቢላዋ ይዘዉ ተመለሡ።ንቧም አበባ የምትቀስመዉ ከዚያዉ አካባቢ ነበር።

3

ንቧም ቦታ ልቀይር አለች እና አሠበች። ከዚያም ያሬድ እና በረከት ንቦቹን የሚያቃጥሉበት ደረቅ እና እርጥብ ገለባ እንደ ችቦ አዘጋጁ። ንቧም ቦታ ሣትቀይር ዝምብላ ታያለች የሚሉትንም ትሠማለች።

4

ንቧም ማሩ ዉስጥ እሾኋን ጨምራበት ነበር። ንቧም እንደዚህ አለች" ምን አለበት ማሬን ብትቀምሣት እና ምላሥህ ቢያብጥ"። ከዚያም ድንገት ማሩ አሥቀናዉና ማሩን በረከት ላሠዉ፡፡ ከዚያም እሾሁ ምላሡ ላይ ተሠካና ምላሡም በጣም አበጠ።

5

ያሬድም እሾሁን እንደምንም ከምላሡ ነቀለለት። ንቧም በደስታ ትፍነከነካለች። ከዛ ያሬድ የበረከትን ምላሥ እያየ እንዳለ ንቧ አንድ ነገር መጣላት ማሩን ቦታ መቀየር። እነሱ ሳያዩዋት ማሩን ቦታ ቀየረችባቸዉ ።

6

ከዚያ ቀና ብለዉ ሢያዩ ማሩ የለም፡፡ ሁለቱም ተያዩ ያሬድ ምን ወሠደዉ? አለ ከዛ በረከት ቀና ብሎ ሲያይ ንቧን አያት።ንቧም እዝ የሚለዉን ድምጿን በደስታ አሽካካችው ። በረከትም ደነገጠ እና ያሬድን ነካ አድርጎ ንቧን አሣየው።

7

ንቧም እዝ የሚለዉን ድምጿን እያሠማች ትዞራቸዋለች፡፡ ከዚያ ያሬድን ንቧ" አንተ ማነህ እና ነው የኔን ማር የምትበላው? "አለችዉ።ያሬድ እና በረከት ሲሮጡ ተከትላ ከጆሮ ከጆሮአቸዉ ላይ ነደፈቻቸዉ። ንቧም ማሯን ሣታሦነካ ቀረች።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ተናዳፊዋ ንብ
Author - ነፃነት ከልካይ
Illustration - ነፃነት ከልካይ
Language - Amharic
Level - First paragraphs