የማህበረሰቡ ጀግኖች
ቅድስት ነጋሽ
ቅድስት ነጋሽ

ዛሬቀኑ ቅዳሜ ነው። የአካባቢያችን ማህበረሰብ በየሳምንቱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ። ዛሬ ደግሞ የመወያያ ዕርእሳቸው የኔጀግና በሚል ነው። ተወካይ ሰብሳቢያችንም እጅ እያወጣ በነፃነት ሀሳባችንን አንድን ገልፅ እድል ይሰጠናል።ማህበረሰቡም እርስ በርሱ ይወያያል።

1

ለመነሻ ያክል አንድ በላይ የተባለ የማህበረሰቡ ነዋሪ እጁን አውጥቶ ሀሳቡን መናገር ቀጠለ ለኔ ጀግና ማለት ደፋር ቆራጥ እና አስተዋይ ሰው ማለት ነው። ሰዉም ትክልክል ነህ እያሉ ለሃሳቡ እያበረታቱ ብዙ እጅ እያወጡ መጡ።ከማሃላቸው።

2

አንዲት በለጡ የምትባል የአካባቢው ግለሰብ መረጣት።እሷም ሀሳቧን ተናገረች።ለኔ ጀግና የምለው ውዷን እናቴን ነው አለች።ምክንያቱም እናቴ ለኔ ስንት ዋጋ ከፍላ ያሳደገችኝ 9 ወር በሆዷ ደግሞ ጡቶቿን አጥብታ ያሳደገችኝ እናቴን ነው።በጀርባዋ አዝናኝ ያኖረችኝንማ አረሳም።

3

የኔ ጀግና እናቴ ናት ብላ ቁጭ አለች።ሰብሳቢውም ከዚህ ለየት የሚል ሃሳብ ያለው ሲል እጄን አውጥቼ ሀሳቤን መናገር ቀጠልኩኝ።ለእኔ ጀግና የምለው አርበኛ ነው ስል ያለ ምክንያት አይደለም። የኢትዮጵያ አርበኞች ጠላትን በአደዋ ተራራ ላይ ድል የነሱ አባቶች ናቸው።

4

እቴጌ ጣይቱ የሴት አውራ የሆነችው ጀግና ህዝቡን በአንድነት አዋዳና አከባብራ በአድዋ ተራራ ላይ ይዛል የወጣች የሴት ጀግና ናት። ምን ይህ ብቻ አፄ ሚኒሊክስ ቢባል የኢትዮጲያ አርበኛ ወፍ እንኳን ስትጮህ ምን አለች የሚል የኢትዮጵያ ጀግና ንጉስ ናቸው።

5

አፄ ቴዎድሮስ በአፉ ጥይት የጠጣ ለእናት ሃገሩ መስዋት የሆነ የጎንደር ንጉስ ናቸው።ብዬ ሃሳቤን ከጨረስኩ በኋላ ማህበረሰቡ በተመስጦ አዳምጠው ስለነበር አዎ ትክክል ነው እያሉ አመስግነው ወደ መጣንበት ተመለስን።

6
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የማህበረሰቡ ጀግኖች
Author - ቅድስት ነጋሽ
Illustration - ቅድስት ነጋሽ
Language - Amharic
Level - First paragraphs