የልደቴ ቀን
እፁብድንቅ ፍቅሩ
Brian Wambi

እለቱ እሁድ ቀን ነበር ።ጄምባ የ8 አመት ልደቷን ለማክበር 2 ቀን ቀርቶታል።

1

ለልደቷም ልብስ፣ጫማ ፣የጆሮጌጥ እና ለልደቷ የተለያዪ ነገሮችን ልትገዛ ከእናቷ ጋር ወደ ገበያ በባጃጅ ሄዱ። ከባጃጁ አንድ ሰው ወረደ። ሰውየው የእጅ ስልኩን ስለረሳው ሮጣ ሰጠችው እና ከረሜላሰጥቶ አመሰገናት።

2

ወደ ገበያ እንደደረሱ አይኗ የገባችውን ቀሚስ እናቷ እንድትገዛላት ዋጋውን ለመጠየቅ ወደ ውስጥ ገቡ ።ሻጯ የተናገረችው ብር በወቅቱ ከፍተኛ ብር ስለነበር እናቷ እንደማትገዛላት ነገረቻት ።ነገርግን ሌላ ከበፊቱ በጣም የምታምር ቀሚስ በርካሽ ዋጋ አገኙናተገዛላት ።

3

እናቷ እጇ ላይ ገንዘብ ስለተረፋት ቆንጆ ጫማ ገዛችላት ።ስላላስቻላት ጫማውን እዛው ገበያ አጠለቀችው።አድርጋ የመጣችውን ጫማ በፌስታል ይዛ ስትሄድ ባዶ እግሯን የምትሄድ ልጅ አይታ እናቷን አስፈቅዳ ሰጠቻት።

4

ልጅቷም በጣም ደስ አላት ።እቤት እንደደረሱ ጄምባ አዲሱን ልብስ ልታስቀምጥ ወደ ሻንጣዋ ስትገባ አሮጌ ልብሷ የለም ነበር ።እናቷ ስትጠይቃት ልታቃጥለው እንደሆነ ነገረቻት ።

5

ነገር ግን ልብሶቹ ከሚቃጠሉ ልብስ ለሌላቸው ሰዎች ቢሰጥ ጥሩ እንደሆነ ለእናቷ ነገረቻት ።በማግስቱም ከአባቷ ጋር ሄዳ ልብስ ለሌላቸው ሰዎች ሰጠች ።በማግስቱም ልደቷን በደመቀ ሁኔታ አከበረች ።

6
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የልደቴ ቀን
Author - እፁብድንቅ ፍቅሩ
Illustration - Brian Wambi, Offei Tettey Eugene, Jesse Breytenbach, Rob Owen
Language - Amharic
Level - First paragraphs