ትጉኋ እናት
እፁብድንቅ ፍቅሩ
እፁብድንቅ ፍቅሩ

በአንዲት ከተማ ውስጥ የሚኖሩ እናት እና ልጅ ነበሩ። እናትየዋ ለልጇ የማትከፍለው መስዋዕትነት አልነበረ ። ከጎረቤት እና ከሰፈር ልጆች እንዳያንስባት የማትችለውን ስራ ሁሉ ትሰራለች።

1

ልጇ አልአዛርም ጎበዝ ተማሪ ነበርና በየአመቱ ስሟንያስጠራል።አልአዛር የ19አመት ልጅ ነበረ።ምግብ ሲበሉ ሆዷን ጥፍንግ አድርጋ ታስርና ሁለት ጉርሻ ጎርሳ ጠገብኩ ትለዋለች።የሰው ቤት እንጀራ እየጋገረች ፣ልብስ እያጠበች ፣የቀን ስራ እየሰራች ልብስ፣ደብተርና ጫማ ትገዛላታለች።

2

ገንዘብ ከየት እንዳመጣች አልአዛር ሲጠይቃት ዘመዳቸው እንደሰጣቸው ትነግረዋለች እናም ያምናት ነበር።ታዲያ አልአዛር ወደ ዩንቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና ተፈትኖ ጥሩ ውጤት አምጥቶ አለፈ።

3

እናቱ በጣም ተቸግራ ነበርና በበፊቱ ስራዋ ቀጥላ ገንዘብ በየ ጊዜው ትልካለች።አልአዛር ተመርቆ ሲመጣ እናቱ ድል ያለ ድግስ ደግሳለች።

4

አሁንም ብሩ ከየት እንደመጣ ሲጠይቃት እንዳያስጨንቃት እና ዛሬ የደስታ ቀኑ እንደሆነ ትነግረዋለች።ስጦታ የወርቅ ሀብል ስትሰጠው አላመነም።

5

ማታም ይህ ሁሉ እንዴት እንደሆነ ጠየቃት እሷም እያለቀሰች ዋሸች።ልጇ አልአዛርም አመናት። የምትዋሸው ልጇ አሁንም ልጅ ስለሚመስላት ነበር።

6

አልአዛር ጥሩ ስራ አገኘ ። ጥሩ ቤት ሰራ ። እናቱን ለልደቱ አምጥቶ በአዲስ ቤት በደስታ እና በተድላ መኖር ጀመረ። ሆኖም ያቺ እናት አሁንም እውነቱን አልተናገረችም ።

7

ልጇም ጥሩ እና የተደላደለ ህይወት ያኖራት ጀመረ ። በዚህም ቀስ ብላ እውነቱን ነገረችው እና አልአዛር ተከፋ አለቀሰ። ነገር ግን ጎበዝ እና ጠንካራ እናት እንዳለው ሲያውቅ ኩራት ተሰማው ። ለእናቱም ይቅርታ አደረገላት።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ትጉኋ እናት
Author - እፁብድንቅ ፍቅሩ
Illustration - እፁብድንቅ ፍቅሩ
Language - Amharic
Level - First paragraphs