ሳራ እና ጀግናዋ
በፅናት ዮናስ
በፅናት ዮናስ

ሣራ የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን እጅግ በጣም ጥሩ ጸባይ ያላት ትሁት፣ አስተዋይ፣መምህራሮቿን አክባሪ የሆነች፣በትምህርቷ የማትደራደር ጎበዝ ተማሪ ናት ሳራ የምታደርገውን ነገር በሙሉ በእቅድ ከፋፍላ የምትጠቀም ጀግና ተማሪ ናት።

1

ሳራ ከሰኞ እስከ አርብ ያወጣቸው እቅድ ትምህርቷ ላይ የሚያተኩር ሲሆን የቅዳሜ እና እሁድ ዋና ዋና እቅዷ ደግሞ ቤተሰቦቿን ማገዝ፣ንጽህናዋን መጠበቅ እና ማጥናት ነው።

2

አንድ ቀን ትምህርት ቤት ክፍል ውስጥ አማርኛ መምህራቸው የኔ ጀግና በሚል ርዕስ ጀግናቸውን ጽፈው እንዲመጡ አዘዘቻቸው።በነጋታውም ሳራ የተሰጣቸውን የቤት ስራ በአግባቡ ሰርታ ለተማሪዎች እና ለመምህራን ለማቅረብ ተዘጋጅታለች ።

3

ብዙ ተማሪዎች ካቀረቡ በኋላ ሳራ የጻፈችውን ጽሁፍ ለማንበብ ወደ መድረክ ወጣች ንግግሯንም እንዲህ በማለት ጀመረ ሀገራችን ብዙ በአለም ላይ ስሟ እንዲጠራ፣እንድትከበር፣ባለታሪክ ሀገር እንድትሆን አጥንትና ደማቸውን ለግሰው ለዛሬዉ ትውልድ አሻራ የጣሉ ብዙ ጀግኖች አሏት።

4

ከነዚህም መካከል ጥቂቶቹ አፄሚኒሊክ፣እቴጌ ጣይቱ እና አፄቴዎድሮስ ና የመሳሰሉት የሀገር ባለውለታ ጀግኖች ናቸው። ከነዚህ የሀገር ባለውለታ ጀግኖች ውጪ የኔ ጀግና እናቴ ናት።እናቴ ጀግናዬ ናት ይልኩት ያለምንም ምክንያት አይደለም እናቴ ጠንካራ፣የማትበገር፣፣ጎበዝ፣ለልጆቿ አርአያ መሆን የምትችል እናትስለሆነች ነው።

5

እናቴ ጀግናዬ ነች ምክንያቱም ለችግሯ እጅ ከመስጠት ይልቅ አስባ እናስተውላ ችግሯን ስለምትፈታ እንዲሁም ልጆችዋን ያለማንም እርዳታ ህፃንነታችን ጀምሮ ልክ እንደ ዘር ጥሩ መሬት ላይ ዘርታ ብቅ እንዳለች ችግኝ ኮትኩታ እና ውሃ አጠጥታ ቀጥ ብሎ እንዳደገው ዛፍ በስነ ምግባር ታንፀናለች።

6

በማንኛውም ጥሩ ሀሳብ ላይ ትደግፈናለች መጥፎ ስንሰራ ተነቅፈናለች እናቴ ለሰዉ ሳይሆን ለራስዋ የምትኖር እውነተኛ ሰው ነች እናቴምንም ቢመጣ በክፉም በደጉም የማትበገር ስለሆነች እናቴ ጀግናዬ፣አርአያዬ፣አስተማሪ፣ጓደኛዬ፣እህቴ ሁሉ ነገር ናት ማለት የጻፈችውን ጽሁፍ ለተማሪዎች እና ለአስተማሪዎች አንብባ አጠናቀቀች።

7

ያቀረበችውን ጽሁፍ መምህሯ እና ተማሪዎች በጣም ወደዱላት እሷም ደስ ብሏት የነገ ህልሟን ለማሳካት ዛሬ ጠንክራ መማር እንዳለባት ተማረች።የሳራ ወላጆችም በባህሪዋ እና በፃፈችው ጽሑፍ ደስተኛ ሆኑ።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሳራ እና ጀግናዋ
Author - በፅናት ዮናስ
Illustration - በፅናት ዮናስ
Language - Amharic
Level - First paragraphs