የማትያስ ደግነት
አቤኔዘር በሪሁን
አቤኔዘር በሪሁን

ማትያስ የሚባል አንድ ልጅ ነበር።ማትያስ ሰውን መርዳት በጣም ይወዳል።የተቸገሩትን እና አዛውንቶች እቃ ተሸክመው ካየ እሩጦ
ሄዳ ላግዛችሁ በማለት ይረዳል።

1

ጓደኞቹንም እንደኔ የተቸገሩትን ሰው እርዱ እድል ይመክራል ።ከለታት በአንድ ቀን እንደተለመደው አንድ እቃ የከበደችው አሮጊት አያና ሊያግዛቸው ሮጥ ብሎ ሄደ እቃውንም በመቀበል ወደ አሮጊቷ ቤት ወሰደላት ካሮጊቷ ግቢ ውስጥ አንድ ሐይለኛ ውሻ ነበር።

2

ውሻውም ማቲያስን እንዳየህ በጣም መጪው ጀመረ።ማቲያስም እቃውን ወደ አሮጊቷ ቤት አስገብ ሲወጣ መውጫው በር ላይ እንደደረሰ ውሻውም የታሰረበትን ገመድ በጥሶ ማቲያስን እግሩን ነከሰው

3

ማትያስም ዋ!ሀ!ሀ!ይ ነከሰኝ እርዱኝ እያለ መጮሁን አላቋረጠም አሮጊቷም ወይኔ ልጄን ወይኔ ልጄን እያሉ ውሻውን አባረሩት።

4

የማትያስ ቤተሰቦቸሰ መጡ ማትያስ በጣም ስለተጎ ስለተጎዳ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ውሻው ጤነኛ ይሁን ተመረመረ።

5

ማቲያስም ለአንድ ሳምንት ሆስፒታል ከረመ ጓደኞቹም የጎረቤት ሰዎችም ሄደው ጠየቁት ማትያስም ተሽሎት ከሆስፒታል ወጣ እናም ማቲያስ ጥሩ ነገር የሰራሁበት ቀን ሲባል ያንን በውሻ የተነከሰበትን ቀን ያስታውሳል።

6
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የማትያስ ደግነት
Author - አቤኔዘር በሪሁን
Illustration - አቤኔዘር በሪሁን
Language - Amharic
Level - First paragraphs