አንባቢው ከድር
አዶንያ በሪሁን
አዶንያ በሪሁን

በድሮ ጊዜ አንድ ከድር የሚባል ሰው ነበር። ይህም ሰው በአነስተኛ ከተማ ውስጥ ይኖር ነበር። ይህም ሰው መፅሀፍ ማንበብ በጣም ይወድ ነበር።

1

ከእለታት አንድ ቀን ቁጭ ብሎ ሲያነብ የተመለከቱት ጓደኞቹ ለምን መፅሀፍ ታነባለህ እያሉ ያዳክሙት ነበር። እሱግን ምንም አይመስለውም ዝምብሎ ያነብ ነበር።

2

ስራ ለመስራት ወደ ስራ ሄዶ ስራውን ሰርቶ ሲመለስ በሰራው ብር መፅሀፍ ገዝቶ ለመምጣት ወደ መፅሀፍ መሸጫ መደብር ሄደና መፅሀፍ ገዝቶ ሲመለስ አንድ አይነስውር ሰው መፅሀፍ ሲያነብ ተመለከተ።

3

በአግራሞት ጠጋ ብሎ ሰውየውን እንዲህ ሲል ጠየቀው" ይቅርታ መፅሀፍ እያነበብክ ነው"።ብሎ ጠየቀው አይነስውሩም ሰው "አዎ እያነበብኩ ነው" በማለት መለሰለት ።

4

ከድርም በአድናቆት"እንዴት ነው የምታነበው"ሲል ጠየቀው።አይነስውሩም ሰው" እኔ የማነበው በእጆቼ እየዳሰስኩ ነው"ሲል መለሰለት።

5

ከድርም አበረታቶት"በርታ ጠንካራ ሰው ነህ "ብሎት ወደ ቤቱ ሄደ።

6
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አንባቢው ከድር
Author - አዶንያ በሪሁን
Illustration - አዶንያ በሪሁን
Language - Amharic
Level - First paragraphs