

በድሮ ጊዜ በአንድ ጫካ ውስጥ የሚኖር አንድ ፍሬያማ ዛፍ ነበረ።በየዓመቱ ያፈራል።ልጆችም እየመጡ ይመገቡት ነበር።በአንድት ወቅት አስማታዊ አሮጊት መጥታ እንዲህ አለችው።
አንተ ዛፍ ለምንድን ነው ለልጆች አፕል የምሰጠው እነሱ ያድጋሉ አንተ ደግሞ ለኔ ጠላት እየሆንክብኝ ነው ስለዚህ ይህንን አፕል ወደ መርዛማ አፕል እለውጠለሁ ልጆችም ተመርዘው ይሞታሉ አለችው።
ፍሬያማው ዛፍም"አይሆንም አንቺ አሮጊት ከፊቴ ዞር በይ ልጆችን መግደል ፍላጎትሽ ከሆነ በኔ መጠቀም ለምን ፈለግሽ አላት።አስማታዊ አሮጊቷም አንተን በጣም ነው የሚወዱህ እኔ ሌላ የሚያምር ወርቃማ ዛፍ ባሳደግ እንኳን አይፈልጉም ስለዚህ ባንተ ነው መጠቀም ያለብን አለችው።
ከዚያም አፕሎቹን ወደ መርዛማ አፕል ለወጠችው ስትለውጠው ፍሬያማው ዛፍ እራሱን ሳተ ልጆችም አፕሉ የሚበስልበት ቀን ዛሬ ነው ብለው ተሰብስበው ሄዱ ሲሄዱ አንዲት ጥቁር ልብስ ና እንጨት የተሠራ ምርኩዝ የያዘች አሮጊት ስትሄድ ተመለከቱ ።
ከዚያ ፍሬማው ዛፍ ሊጠይቁት ሲሄዱ ፍሬያማው ዛፍም ራሱን ስቶ አልተነሳም ነበር።ልጆቹም"እንቅልፍ ይዞ ነውእንዴት አንቀስቅሰው አሉ።ከዚያም አፕል መብላት ስላማቸው አፕሉን ቆረጡ ሲቆርጡ ያንንም ጊዜ ፍሬያማው ዛፍ አልተነሳም ነበር።
አንዱ ከሁሉም ቀድሞ በላ ትንሽ ቆየት ብሎ ራሱን ወደቀ ሁሉምሊበሉት የነበረውን አፕል ጥለው"ጓደኛዬ ጓደኛዬ ምን ሆነህ ነው ማለት ጀመሩ።ፍሬያማው ዛፍም ተነሳና"ምን ሆነ ጓደኛዬ አለ።
እነሱም አንተ ነህ ለዚህ ሁሉ ጥፋተኛባንተ ጥፋተኛው በአንተ አፕል ምክንያት ጓደኛችንን አጥተነው ነበር።ስለዚህ አንተን አንፈልግህም ከአሁን በኋላ አንመጣም ብለው ትተውት ሄዱ።ከሁሉም አንዱ ቀርቶ ነበር።
ጓደኛዬ እስከዛሬ የምሰጠን አፕል እኛን የሚያሳድገን ነበር። መርዛማ አፕል ሰጠኸን አለው።ፍሬያማው ዛፍም ጓደኛዬ ያቺ አስማታዊ አሮጊት ናት አንተ ጠላቴ ነህ።አፕሎቼን መርዛማ ያደረገችብኝ።ከአሁን በኋላ በየዓመቱ መጣለች።
ስለዚህ በአንድ ነገር ተስማምተን አንድ ነገር ፈጥረን ለምን አንገላትም አለ።ጓደኛውም አዎ መግደል አለብን እኔ ለጓደኞቼ እነግራቸዋለሁ አለ።ተነጋግረው አስማታዊ አሮጊቷ መጥታ ፍሬያማውዛፍን ስታወራው ከኋላ ማጅራቷን ብለው ገደሏት።
ፍሬያማው ዛፍ ወደ የሚያምር ለአይን የሚያጓጓ ጣፋጭ ወደ ሚያፈራ ዛፍ ተለወጠ።ጓደኛውም ከዳነ በኋላ በሰላም መኖር ጀመሩ።

