

ከዕለታት አንድ ቀን ቀኑ ቅዳሜ ነበር።አንዲት መክሊት የምትባል ልጅ ነበረች።መክሊትም እናቷ ጋር ሄዳ እንዲህ ብላ ጠየቀቻት«እማዬ ዛሬ ማርያም ስለሆነ ከጓደኞቼ ጋር አብሬ ቤተክርስትያን ልሂድ አለቻት»
እናቷም እሺ ቶሎ ደርሰሽ ነይ እንዳትቆይ አለቻት።መክሊትም ጓደኞቿን ጠርታ መንገድ ጀመሩ።
ወዲያውኑ ቤተክርስቲያን ደረሱ።ከደረሱ
በኋላ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንድ ደካማ አባት እየለመኑ አየች።መክሊትም በጣምአሳዘኗትናጓደኞቻን ከያዝነው ብር ላይ ለምን አሰጣቸውም አለቻቸው እነሱም ግን በሀሳቧ ሊስማሙ አልቻሉም ነበር።
መክሊትም ለምንድን ነው በሀሳቤ ያልተስማማችሁ እነዚህ አባት የእናንተ አባት ቢሆኑም ኖሮ ጥላችኋቸው ታልፉ ነበር ።ብላ ጠየቀቻቸው? የመክሊክ ጓደኞች ያልሽው ትክክል ነው።
ለዚህ አባት ካላችሁ ላይ ብታካፍሏቸው ምርቃት ታገኛላችሁ፤በእግዚአብሔርም ዘንድ ምህረት ታገኛላችሁ።ጓደኞቿም አንቺ ትክክል ነሽ ይቅርታ አድርጊልን።ተፀፅተናል ከጥፋታችንም ተምረናል አሏት።መክሊትም አሁኑኑ ሄደን ካለን ብርላይ እናካፍላቸው አለቻቸው።ወዲያውኑ ሄደው።
ከያዙት ብር ላይ ካካፈሏቸው በኋላ ምርቃት ተመርቀው ወደ ቤታቸው መሄድ ጀመሩ።ቤታም ከደረሰች በኋላ ጓደኞቿ ቻው ብላ ወደ ቤት ገባች እናቷም ቤተክርስቲያን ጥሩ ቀን አሳለፍሽ ብላ መክሊት ጠየቀቻት? መክሊትም የሰራችውን ጥሩ ስራ ነገረቻት።
ጓደኞቿ ከመጥፎ ሀሳብ ወደጥሩ ሀሳብ እንዲቀየሩ መምከሩ ነገረቻት መክሊትም ዛሬ ጥሩ ነገር የሰራሁበት ቀን መሆኑን ነገረቻት። የመክሊት እናት በጣምተ ደስታ መክሊትን አቅፋ ሳመቻት በሰራችው ጥሩ ስራ በጣም ተደሰተች።

