

በአንድ ወቀት በቤተ-መንግሰቱ የጓሮ ስፍራ ወርቃማ ፍሬ የሚሰጥ የብርቱካን ዛፍ ያለው ንጉሥ ነበር። የብርቱካኑ የዛፍ ፍሬ በደረሰ ሰዐት በየአንዳንዱ ምሽት አንድ አንድ ፍሬ እየተሠረቀ ያድራል ።
ይህ ሁኔታ ሲደጋገም ንጉሱ እጅጉን በጣም ተቆጡ። አትክልተኛዉን አስጠርተው ምሽቱን ሙሉ ጥበቃ በማድረግ ሌባዉን እንዲደረስበት ትዕዛዝ አስተላለፉ።
የአትክልተኛዉ የበኩር ልጁን የብርቱካን ዛፉን እየጠበቀ የሚሰርቀዉን ሌባ እንዲይዝ አዘዘው።ሆኖም ለሊቱ አጋማሽ ላይ በእንቅልፍ ተሸነፈ። አንድ ፍሬ ወርቃማ ብርቱካን ተሰርቆ አደረ። አሁንም ንጉሱ ተበሳጭተው እንደዚህ ሲሉ ተናገሯቸው።
እንዴት ይሄንን ሌባ ተከታትሎ መድረስ ያቅታችኋል ሲል በጩኸት እና ንዴት በተቀላቀለ ስሜት ተናገራቸዉ።አሁንም በሚቀጥለዉ ቀን የአትክልተኛዉ ሁለተኛ ልጅ ሀላፊነቱን ወስዶ ሲጠብቅ አደረ።
ከእኩለ ለሊት በኋላ ሙሉ አካሏ ከወርቅ የተሰራች እርግብ እየበረረች መጥታ አንዲት የብርቱካን ፍሬ ልትቀጥፍ ስትሞክር ልጁ አስወነጨፈባት። ሆኖም ሳትሞት አንድ ወርቃማ ላባ ብቻ ጥላ በረረች።
በሚቀጥለዉ ማለዳ ይህችው የወርቅ ላባ ለንጉሱ ቀረበች። አንዷ የወርቅ ላባ ዋጋ ከእሳቸዉ ንጉሳዊ ሙሉ ሀብት እንደሚበልጥ ተገንዝበው አንድ የወርቅ ላባ ብቻ ሳይሆን ወርቃማዋን ወፍ ይዘዉ እንዲመጡላቸዉ አዘዙ። ፍለጋዉ ተጧጧፈ።
የአትክልተኛዉ የበኩር ልጅ ለፍለጋ በወጣበት ጊዜ በጫካ ዉስጥ አንድ ተኩላ አገኘ። ቀስቱን አነጣጥሮ ሊያስወነጭፍበት ሲሞክር ግን ተኩላዉ አትግደለኝ ወርቃማዋን እርግብ እንድታገኝ በምክር አረዳሀለሁ ሲል ተማፀነዉ።
ወርቃማዋን እርግብ እንደምትፈልግ አዉቃለሁ። በምሽት በዚህ ተራራ ጀርባ ወዳለዉ መንደር ሂድ። ስትደርስ አንደኛው ለእይታ የሚስብ አንደኛው ደግሞ ለእይታ የሚከብድ ቤቶች አሉ።
እንዴት ይሄ ቀበሮ ከኔ በልጦ ለኔ የሚያስረዳው ብሎ በንቀት ወደሌላ ቦታ መሄዱን ቀጠለ።ብዙ መንገድ ከተጓዘ በኋላ አንድ የወዳደቀ ቤት ተመለከተ። ወደ ውስጥም ሲገባ አስፈሪ የሆኑ ለሰው ልጅ ጎጂ የሆኑ መንፈሶች አየ።
ልክ ሊያመልጥ ሲል በሩ ተዘጋ። ምንም ያክል ለማምለጥ ቢሞክር ሳይሳካለት ቀረ። የዘበኛው ሁለተኛ ልጅ የሆነው የወንድሙን ጩኸት ሲሰማ ወዳለበት በፍጥነት ተጓዘ ።ወንድሙን ሲመለከተው በአስፈሪ መናፍስት እየተሠቃየ ነው።
እግረ መንገዱን ወደ ቤቱ ዘልቆ ገባና ወንድሙን ከጥፋት ታደገው። ያችን ሲፈልጉ የነበረችውን እርግብ ተመለከቱ።
በፍጥነት ወደ ምትሄድበት ቦታ ተከትለው ሄዱ።ከ አንድ ቤት ጣራ ለይ አረፈች እርግቧንም ያዟት።
ለንጉሱም ቀረበች ንጉሱ ይሄንን ነገር ሲያዩ ጊዜ በአግራሞት በእንደዚህ ሁኔታ መታለላቸው ገርሟቸው ከት በለው ሳቁ።

