

በአንድ ጫካ ዉስጥ በህብረት የሚኖሩ አራት ላሞች ነበሩ። እናም እነዚህ ላሞች ሁል ጊዜ ይተጋገዛሉ። በጫካዉ ውስጥ አስፈሪ ትልቅ እና ሀይለኛ ነብር ነበር። ይሄም ነብር አራቱን ላሞች ለመብላት በጣም ይፈልግ ነበር።
ግን እነሱ ሁሌም ቢሆን ስለሚተባበሩ እና ስለሚተጋገዙ አንድም ቀን ተሸንፈው አያውቁም። ነብሩ ሁል ጊዜ አራቱ ላሞች ጋር እየሄደ ይተናኮላቸው ነበር። ላሞቹም ግን በህብረትና በአንድነት ሆነው በቀንዳቸው እየወጉ ያባርሩት ነበር።
በዚህም ስራቸው ነብሩ በጣም ይናደድ ነበር። በዚህም ሁኔታ ነብሩ እየጓጓ ላሞቹም እየፈሩ ብዙ ቀናቶች አለፉ። ከእለታትም አንድ ቀን ላሞቹ በተለያየ ምክንያት ተጣሉ።
የተጣሉበትም ምክንያት አንዷ ላም የሆነ የሚያምር አረንጓዴ ሳር አየች። ከዛም ጓደኞቿን እስከዛሬ አብረዉ ስለነበር የሚበሉት አሁን ግን እኔ ብቻዬን ነው የምበለው አለችና ራስ ወዳድ ሆና በዚህ ምክንያት ሳሩን ከጓደኞቿ አብልጣ ሄደች።
በዚህም ምክንያት ተጣልተው ሶስቱ ላሞች ብቻ ቀሩ። እናም በቀጣዩ ቀን ደግሞ ሁለተኛዋ ሌላ አዲስ ጓደኛ ተዋውቃ ሁለቱን ጓደኞቿን ትታቸው መሄድ ጀመረች። ከዛም ሁለቱ በጣም ተናደዱ።
በሌላኛው ቀን ደግሞ ሁለቱ ላሞች ለምን እኛስ አንለያይም አብሮተታችን ጎዳን እንጂ አልጠቀመንም አሉና ሁሉም ብትንትናቸው ወጣ። ከዛም በኋላ አራቱም ላሞች በተለያየ እቅጣጫ ሳር ይግጡ ጀመሩ።
ነብሩም አንድ ቀን በጫካዉ ውስጥ ሲያልፍ አንዷ ላም ብቻዋን ስትግጥ አያት። እናም እንዲህ አለ በጣም ደስ ይላል አንዷ ላም ከሆነች ሁሉም ተለያይተዋል ማለት ነዉ ብሎበጣም ተደሰተ።
ከዛም አሁን ስለተለያዩ እያንዳንዳቸው አድኜ መብላት አለብኝ አለና ከራሱ ጋር ማውራት ጀመረ። ግን የመጀመሪያዋ ላም ብቻዋን ሳር ስትግጥ ቅርቅር ይላታል። እናም ስታስበው ግን እኛ እኮ መተባበራችን ይጠቅመን ይመስለኛል አለች።
እናም አሁን ሄጄ ለሁሉም አሁን ስለተጣላን እንደድሯችን መታረቅ ይኖርብናል። እናም እያንዳንዱ ጋር ሄዳ ብንታረቅስ ስትላቸዉ ሁሉም ሀሳባቸውን ተነጋግረው እና ተስማምተው በደስታ ታረቁ።
ይሄንን ያላየ ነብር እቤቱ ሆኖ ይጎመጃል። እያንዳንዱን ሊበላቸው ሲሄድ ሁሉም በአንድ ላይ አራት ሆነው ሳር ሲግጡ አገኛቸው። በዚህም በጣም እና ተስፍ ቆርጦ ተመለሰ።
አንዷ ላም አያ ነብሮ አትልፍ እኛ ትንሽ ጊዜያት ተጣልተን ነበር። ነገር ግን ሳይረፍድ መልሰን መተባበራችንን አጠናክረነዋል እንጂ መጣላታችንን አልቀጠልነውም አለችው።
ይሄንን ስትለው ነብሩ በጣም ተናዶ ተነስቶ ሊበላት ሲል ተጋግዘው አሸንፈው ጣሉት። መተባበራችን ይጠቅመናል እንጂ አይጎዳንም ከዚህ በኋላ መቼም መጣላት የለብንም ተባብለው በአንድነት እና በሰላም መኖር ጀመሩ።

