ተራማጁ እባብ
ራሔል ግዛቸዉ
ራሔል ግዛቸዉ

በዱሮ ጊዜ በአንድ ጫካ ውስጥ ብዙ እንስሳት ይኖሩ ነበር ።ከነዚያ ወስጥ ደግሞ ተራማጁ እባብ አንዱ ነበር ።በዚያ ጫካ ውስጥ አስማተኛ ሰውዬ ነበር። ተራማጁ እባብ እግሮቹ ልክ እንደ ድንጋይ ስለነበሩ ሲራመድ ድምፅ ያወጡበታል።

1

ምግብ የሚያገኝበት ብልሀትም የለውም። በጫካ ውስጥ ያሉ እንስሳት በሙሉ እባቡ እንደመጣ በእግሩ ድምፅ ይለያሉ።የእግሮቹን ድምፅ እየሰሙ ሌሎች እንስሳት ይሸሹታል።

2

በዚህ ምክንያት ከጫካ ወጥቶ ሰዎች መንደር ሄዶ ነበር ምግብ የሚበላው፡፡ ሰዎች ሲደርሱበት ሮጦ ያመልጣል።እግሮቹን ግን አንድ ቀንም አመስግኗቸው አያቅም በተቃራኒው ያማረራቸው ነበር።

3

አንድ ቀን አንዲት የወፍ ጫጬት አይቶ ሊበላት ጠጋ ሲል ጫጩቷ የእግሩን ድምጽ ሰምታ በረረች፡፡ እባቡም በጣም ተናዶ እያማረረም መንገዱን ቀጠለ ፡፡በመንገዱ ላይ ምን እንደሚያደርግ እያሰበ አያ ቀበሮን አገኘው።

4

ከቀበሮ ጋር ጓደኛሞች ነበሩ።"ሰላም ነው ጓደኛዬ" አለው ቀበሮ።እባብም ''ምን ሰላም አለ " አለ።"ምን ይሄ እግሬ እኮ ድምፅ እያወጣ የምበላውን ነገር አሳጣኝ ፡፡ በዛ ላይ እንደናንተ ምግብ የማገኝበት ብልሀት የለኝም ኡፍ መረረኝ "አለ እባብ በሀዘኔታ።

5

ቀበሮም አይ......እያለ ከዛም አንድ ሀሳብ መጣለት ።"ለምን አስማተኛው ሰውዬ ጋር አትሄድም እሱ መፍትሄ ሊሰጥህ ይችላል" አለ።እባቡም "አመሰግናለሁ ጓደኛዬ ጥሩ ሀሳብ ነው ያመጣኸው "አለውና ተለያዩ።

6

ተራማጁ እባብም ቀስ ብሎ ለመራመድ እየሞከረ አስማተኛው ሰውዬ ጋር ደረሰ።አስማተኛው ሰውዬ እንዲገባ ነገረው ፡፡ከዛ ለምንድነው የመጣኸው ብሎ አስማተኛው ሰውዬ ጠየቀው፡፡እባቡም እግሮቼ በጣም እያሰቸገሩኝ ነው አለው።

7

"ልበላቸው የምፈልገጋቸው እንሰሳቶች በእግሬ ድምፅ የተነሳ ጥለውኝ ይሸሻሉ ።በዛ ላይ የሚይዝበት ብልሀት የለኝም "አለው።አስማተኛው ሰውዬም "እና ምንድን ነው የምትፈልገው "አለው፡ ፡

8

"ብልሀተኛ እንድሆን እና የእግሮቼን ድምፅ እንድትቀንስልኝ ነው "አለ እባብ።አስማተኛው ሰውዬም ''የእግሮችህን ድምፅ መቀነስ አልችልም ፡፡ግን ምንም እግር ሳይኖርህ መጓዝ እንድትችል እና ብልሀተኛ እንድትሆን ማድረግ እችላለሁ ''አለው፡፡

9

እባቡም ''እሺ እንደዛ መሆን ይችላል"አለ።እናም ከዛ በኋላ በደረቱ የሚሳብ እና ብልሀተኛ አዳኝ ሆነ ።ነገር ግን መሸሽ ስለማይችል ሰዎች ባገኙት ቁጥር ይደበድቡታል ፣ ይቀጠቅጡታል።እባብም የሚሳበው በደረቱ ስለሆነ ጫካው ፀጥ ያለ ሆነ።

10
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ተራማጁ እባብ
Author - ራሔል ግዛቸዉ
Illustration - ራሔል ግዛቸዉ
Language - Amharic
Level - First paragraphs