ደስተኛዋ ልዕልት
ራሔል ግዛቸዉ
ራሔል ግዛቸዉ

በድሮ ጊዜ በአንድ ሀገር ዉስጥ ንጉስ ቻርለስ እና ልዕልት አና የሚባሉ አባት እና ልጅ ሀገሪቱን እያስተዳደሩ በቤተ መንግስት ውስጥ ይኖሩ ነበር።

1

ሀገሪቱ በሸክላ ስራ እና ሽያጭ የታወቀች ነበረች።ንጉሱም ስራ ስለሚበዛበት ለልጁ ጊዜ ስለማይሰጣት በጣም ትናደድ ነበር።

2

ልዕልት አና ሸክላ መስራት በጣም ትወዳለች፡፡ ነገር ግን የአባቷን እና የራሷን ክብር ዝቅ ያደርጋል ብላ ስለምታስብ በድብቅ ክፍል ውስጥ ትሰራ ነበር። በዚህም ምክንያት ደስተኛ አልነበረችም።

3

በአንድ ወቅት የሀገሪቱ የሽክላ ስራ ሽያጭ ቀነሰ ንጉሱም በጣም ተጨነቁ።ልዕልቷም አባቷ ሲጨነቅ ባየችው ጊዜ ጠባቂዎቿን በድብቅ ቀይ አፈር እንዲያመጡላት አዘዘች።

4

ጠባቂዎቹም አፈሩን አመጡላት። ከዚያም በተለያዪ ዲዛይኖች የተለያዪ ሸክላዎችን ሰራች።ከደረቁ በህዋላ እንዲሸጧቸው አደረገች።ንጉሱም ይህን ባዩ ጊዜ ተገርመው "ማነው እንደዚህ የሚያደርገው?" እያሉ ከአማካሪዎቻቸው ጋር ይነጋገሩ ጀመር። ለብዙ ጊዜ ልዕልቷ እንደዛ እያደረገች ቆየች።

5

አንድ ቀን ጠባቂዎቹ እንደ ለመዱት ቀይ አፈር በድብቅ ወደ ቤተ መንግስቱ ይዘው ሲገቡ አንዱ ጆንያ ተቀዶ ሰለነበር እየፈሰሰ ነበረ።

6

ጠባቂዎቹ ግን አላዩትም ዝምብለው ድብቁ ክፍል ይዘው ሄዱ።ነገር ግን አንዱ የንጉስ አማካሪ ይህን ተመልክቶ ስለነበረ ለንጉሱ ሄዶ ነገረው። ንጉሱ ከአማካሪያቸው ጋር አፈሩ የሰራውን መስመር ተከትለው ሄዱ።

7

ሲደርሱም ልዕልት አና በአፈሩ የተለየ ሸክላ እየሰራች ተመለከቱ። ንጉሡም በጣም ደነገጠ ከዛም ልጁን በደንብ አቀፋት ደስ አለው ደግሞም ከፋው። ደስ ያለው ልጁ እንዲህ ያለ ችሎታ ስላላት ነበር። የከፋው ደግሞ ለልጁ ጊዜ አለመስጠቱ እና እንደዚህ ያለ ችሎታ እያላት እሱን ፈርታ በድብቅ ሸክላዎቹን መስራቷ ነበር።

8

ከዚያም በኋላ ንጉሥ ከልጁ ጋር አብረው የሚሰሩ ሰዎችን በመቅጠር በብዛት አፈር እንዲያመጡላቸው እና እንዲሰሩ አደረገ።

9

የሀገሪቱ የሸክላ ስራ እና ሽያጭ ጨመረ።ንጉሡም ለልጁ ጊዜ መስጠት ቀጠለ።ልዕልት አና በጣም ደስተኛ ሆነች።

10
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ደስተኛዋ ልዕልት
Author - ራሔል ግዛቸዉ
Illustration - ራሔል ግዛቸዉ
Language - Amharic
Level - First paragraphs