የሀረጓ ትል
ሀና በለጠ
ሀና በለጠ

በድሮ ጊዜ በአንድ ጫካ ውስጥ በአንድ ሀረግ ላይ ይኖሩ የነበሩ ሁለት ትሎች ነበሩ።አንደኛዋ ትል እሙ ትባል ነበር፡፡ ሌላው ደግሞ አቡሌ ይባል ነበር።እሙ እና አቡሌ በጣም ይዋደዱ ነበር፡፡

1

ከዚያም በኋላ ተጋቡና ልጅ ወለዱ፡፡ ስሟንም ሚጡ አሏት።ሚጡም በትምህርቷ ጠንካራና ታታሪ የሆነች ትል ነበረች።ነገር ግን በአሁኑ ዓመት ሚጡ በትምህርቷ ተፎካካሪ መጣባት። የተፎካካሪዋም ስም ቹቹ ይባላል።ሚጡም የመንፈስ ቅናት አደረባት።

2

እናም እንዳይበልጣት በደንብ ማጥናት ቀጠለች፡፡ በዚያም ዓመት አንደኛ ወጣች።ቹቹም ከተፎካካሪው ሚጡ ጋር ለመጣላት ወሠነ እናም ተጣላት።ሚጡም የምትማርበትን ክፍል ሳትቀይር ትምህርቷን ቀጠለች ። የቹቹ ቤተሰቦችም ልጃችን ለምን ዝቅተኛ ውጤት አመጣ በማለት ወደ ትምህርት ቤት ሄዱና መምህሩን አናገሩ።

3

መምህሩም ቹቹ ያደረገውን ነገር ሁሉ ነገራቸው።የቹቹ እናትም ይህንን በሰሙ ጊዜ ልጃቸውን ለብቻው ወስደው መከሩት።"ቹቹ እንደዚህ ማድረግ የለብህም "አሉት።እናም አሁን ይቅርታ ጠይቅ ብለው ላኩት። ሚጡም ይቅርታውን ተቀበለች ።ጓደኛሞችም ሆኑ ከዚያም አንድ ላይ በማጥናት ሁለቱም አንደኛ ወጡ።

4
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የሀረጓ ትል
Author - ሀና በለጠ
Illustration - ሀና በለጠ, አቤኔዘር በሪሁን
Language - Amharic
Level - First paragraphs