

በድሮ ጊዜ እንዲት ቀበጥ ድመት ነበረች።ድመቷም አታድርጊ የተባለችውን ነገር ማድረግ ትወዳለች።በዚህም የተነሳ የሰፈሩ ሰዎች በጣም ይናደዱባት ነበር።
አንድ ቀን ጠዋት ቀበጧ ድመት እንደተለመደው ተንኮል ለመስራት አቅዳ ከቤቷ ወጣች።ትንሽ ከተጓዘች በኋላ አንድ አሮጊት በማዳበሪያ ሙሉ አፕል ተሸክማ አየቻት።
ቀበጧ ድመትም ያቺ አሮጊት አፕሉ እንደከበዳት አይታ ቀሚሷን ረግጣ አፕሉን እንድትጥለው አደረገቻት።አሮጊቷም ወደቀች ፡፡በዚያን ጊዜ ድንጋይ ጭንቅላቷን መታት።ቀበጧ ድመትም ማዳበሪያውን ፈትታ አፕሉን ሰርቃ ሄደች።
በነጋታውም ጠዋት የተንኮል ዕቅድ አውጥታ ከቤቷ ወጣች።በመንገድ ላይ የነበረ አንድ ሰውዬ ስልኩን ሲያወጣ የብሩ ዋሌት አብሮት ወጥቶ መሬት ላይ ወደቀ ፡፡ሰውዬውም አላየውም ነበር።
ነገር ግን ቀበጧ ድመት አይታው ስለነበር ቶሎ ብላ አንስታ ብር መኖርና አለመኖሩን አየች፡፡ ዋሌቱም መቶ ብር ነበረው።በመቶ ብሩ ስጋ ገዝታ ወደ ቤቷ እየተመለሰች ሳለ በፌስታል የያዘችውን ስጋ ስታወዛውዝ አጠገብዋ የነበረው ትልቅ ዛፍ ላይ ተንጠለጠለ ።
ቀበጧ ድመትም እዛ ትልቅ ዛፍ ላይ እንደምንም ብላ ወጥታ ለማውረድ ስትል መሬቱን አዘቅዝቃ አየችው።በጣምም አዞራት ፤ማውረድም አቃታት ፡፡እሷም ሰው እንዲደርስላት ብላ "ሚያው፣ሚያው "አለች።ነገር ግን በአጠገቧ የሚያልፉ ሰዎች እንዲህ አሏት።
"እሰይ አንቺ ተንኮለኛ ድመት"እያሉ ሳቁባት።ተንኮል ምንም ጥቅም እንደሌለው አወቀች።በመንገድ ላይ የነበረ አንድ ሰውዬ የእርዳታ ጥሪዋን ሰምቶ አያትና
"ውይ ይቺ ምስኪን ድመት "በማለት መሰላል አምጥቶ አወረዳት።
ከጥፋቷ ታርማም ታማኝ፣ሩህሩህ እና ጎበዝ ሆና የአዛውንት ምርቃት ፈሰሰላት።ቀበጧ ድመት የሚለውን ስሟን ቀይረው ጎበዟ ድመት በማለት ስም አወጡላት።ድመቷም በታማኝነት ማገልገል ጀመረች።

