ሮቤል እና አድዋ
ራኬብ ታምራት
Rakeb Tamrat

ከዕለታት በአንድ ቀን በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚማር ሮቤል የተባለ ልጅ ነበር። አንድ ቀን አካባቢ ሳይንስ መምህራቸው ስለ አድዋ ምንነት እና የተለያዩ ነገሮች ጠይቀው፣አንብበው ወይም ከተለያዩ የመረጃ ምንጮችአሰባስበው እንዲመጡ አዘዟቸው።

1

ሮቤልም በረፍት ሰዓት ጨዋታው ምንም ሳያጓጓው የተሰጠውን የቤት ስራ ለመስራት ከተለያዩ መፅሀፍ ማንበብ እንዳለበት ስለሚያውቅ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ወደ ሚገኝ ቤተ-መፅሐፍት ሔዶ ካነበበው እንዲህ በማለት አጠናክሮ ፃፈ።

2

«አድዋ ምርት በ1888 ዓ,ም በየካቲት 23 ቀን ጦርነት የተካሄደበት እና ኢትዮጵያ ድል ያገኘችበት ቦታ ሲሆን ጦርነቱም የተካሄደው በጣሊያን እና በኢትዮጵያ መካከል ነበር። »ለጦርነቱ መንስኤ ጣሊያን ለኢትዮጵያ ከላከችው 20 አንቀፅ 17 ኛውን አንቀፅ የአማርኛ እና የጣሊያንኛ ቋንቋ መለያየት ነበር።

3

አንቶሎኒ በተገኘበት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ 17 ኛው አንቀፅ ይቀየር (ይሻሻል) ይህንን አንቀፅ አንቀበልም አሉ።የጣሊያኑ አንቶሎኒ አይሆንም በማለት እምቢኝታውን አሰማ። በዚህ ሰዓት ክርክር ተነሳና አንቶሎኒ ጦርነት ይኖራል አለ።

4

ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ በየከተማው በአዋጅ ነጋሪ ነጋሪት ተጎስሞ እንዲታወጅ አደረጉ።በቀጠሯቸውም ቀን የካቲት 23 በአድዋ ተራራ ላይ ተገናኝተው ጦርነቱም በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።ኢትዮጵያ ለማሸነፏ ምክንያት የሆኑት እነዚህ ናቸው፡-

5

1ኛ፦እቴጌ ጣይቱ ብጡል ውሀው እንዲያዝ በማድረጓ በውሀ ጥም ብዙ የጣሊያን ጦር ሞተ።
2ኛ፦እዛው በዛው መድፍ ከጣሊያን በመማረክ በዛው መድፍ ብዙ የጣሊያን ሰራዊት ሞተ።
3ኛ፦እና የመጨረሻው አንዱ ከአንዱ መተሳሰቡና መዋደዱ ነው» ብሎ አጠናቀቀ።

6

በነጋታውም መምህሩ አነበበውና ከየት እንዳመጣው ጠየቀው፡፡ አንብቦ እንደሆነ ነገረው።መምህሩም ደስ አለው።ማበረታቻ መፅሀፍ ሸለመው።

7

ልጁ በማንበቡ ቀጥሎ በመካኒካል ኢንጂነሪንግ ተመርቆ አሁን የማንበብ ባህልን የሚያበረታታ ቤተ መፅሀፍት ከፍቶ ይገኛል።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሮቤል እና አድዋ
Author - ራኬብ ታምራት
Illustration - Rakeb Tamrat
Language - Amharic
Level - First paragraphs