ጀግናው አባት
ሀይማኖት መላኩ
መላኩ የሺጌታ

የኔ ጀግና አባቴ አቶ መኮንን ካሣ ይባላል፡፡ ጀግናዬ የሆነበት ምክንያት ገና በወጣትነቱ በ1970 ዓ.ም በ15 ዓመቱ በቀረበው የእናት ሀገር ጥሪ ከጓደኞቹ ጋር በውትድርና ሞያ ላይ በመሰማራቱ ነው።

1

በምሥራቅ ኢትዮጵያ ክፍል በመዝመት ከወራሪ የሶማሊያ ጦር ጋር ባደረገው ከፍተኛ ውጊያ የሶማልያ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ዘልቀው በመገባት የያዙትን የኢትዮጵያ ከተሞች አስለቅቋል።

2

በውጊያ ላይ እያለ በተደጋጋሚ በጠላት ጥይት ተመቶ ሁለት አይኑንና አንድ እግሩን አጥቷል።

3

ይሁን እንጂ አልበገርም በማለት ትምህርቱን ከስምንተኛ ክፍል በመቀጠል በህግ ሞያ ማስትሬቱን ይዛል።

4

ከዛም በተማረው ሙያ መሰረት በመንግስት ስራ ላይ ተሰማርቶ ይሰራ ጀመር።

5

ከእለታት አንድ ቀን እናታችንን አግብቶ ወንድሜን ወልደው በንክብካቤ አሳድገዋል።

6

ከዛም እኔ ስለተወለድኩ የሚከታተለውን ህክምና ትቶ ተስፋ ባለመቁረጥ እድሜው ጡረታ የሚያስወጣው ቢሆንም እኔን እየተንከባከበ እና እያስተማረ ይገኛል።

7

ቢሆንም አሁን ግን ህመሙ ስለበረታበት በ2017 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ሄዶ በህክምና ላይ ይገኛል።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ጀግናው አባት
Author - ሀይማኖት መላኩ
Illustration - መላኩ የሺጌታ
Language - Amharic
Level - First paragraphs