ሮቤል እና አድዋ
ራኬብ ታምራት
Isaac Okwir

ከዕለታት በአንድ ቀን በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚማር ሮቤል የተባለ ልጅ ነበር ከዕለታት አንድ ቀን አካባቢ ሳይንስ መምህራቸው ስለ አድዋ ምንነት እና የተለያዩ ነገሮች አንብበው ወይም ከ ተለያዩመሰጃ ምንጮች አሰባስሰበው እንዲመጡ አዘዟቸው።

1

ሮቤልም ካነበበው እንዲህ ሲል ፃፈ «አድዋ ማለት በ1888ዓ.ም የተካሄደ ጦርነት ነበር። መንስኤው ደግሞ ጣሊያን የኢትዮጵያን ቅርስ ለመውረስ ከላከቸው 20 አንቀፅ 17ኛው አንቀፅ አማረኛ እና ጣሊያነኛ ቋንቋ መለያየት ነበረ ከዛን ዶግማዊ አፄ ሚኒሊክ 17ኛው አንቀፅ ይቀደድ ሲሉ ጣሊያን አይቻልም አለች ከዛን ጦርነት ታወጀ።»

2

«በቀጠሯቸውም ቀን አድዋ ተራራ ላይ ተገናኙ ጦርነቱም ተካሄደ ጦርነቱም በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቀቀ ለማሸነፋቸውም ምክንያት የሆኑት እነዚህ ናቸው
1ኛ= የሴቶች እርዳታ ነው 2ኛ =ከጣሊያን መድፍ እንዲማረክ በማድረግ በዛው መድፍ ብዙ የጣሊያን ሕዝብ ገደለች 3ኛው= እና የመጨረሻው ሕዝቡ መተሳሰቡና ፍቅሩ ነው » ብሎ አጠናቀቀ።

3

በነጋታውም ለመምህሩ ሰጠው መምህሩም በመደነቅ ከየት እንዳመጣው ጠየቀው ሮቤልም አንብቦ እንደሆነ አስረዳው መምህሩም አንባቢ ትውልድ በመፈጠሩ ደስ እየተሰኘ ማበረታቻ ይሆናል በማለት እነሆ ጀግና የሚለውን መፅሀፍ ሸለሙት። ልጁ በመካኒካል ኢንጂነሪን ትምህርቱን ጨርሶ አሁን የማንበብ ባህልን የሚያበረታታ ቤተ መፅሀፍ ከፍቶ ልጆችን የሚያበረታታ መፅሀፍ አሳተመ።

4
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሮቤል እና አድዋ
Author - ራኬብ ታምራት
Illustration - Isaac Okwir
Language - Amharic
Level - First paragraphs