

በድሮ ጊዜ በአንድ ከተማ ዉስጥ የሚኖሩ ሶስት በጣም የሚዋደዱ ቢራቢሮዎች ነበሩ። ነገር ግን ሶስቱም ቢራቢሮዎች የተለያየ መልክና ቀለም ነበራቸው። ከእለታት አንድ ቀን ሶስቱም ቢራቢሮዎች አንድ ጋር በአንድነት እየሄዱ እያለ በጣም ከባድ ዝናብ መምጣት ጀመረ።
ከሶስቱ ቢራቢሮዎች መካከል ቢጫ ቀለም ያለው አንድ ቢራቢሮ ዝናብ እስከሚያቆም ድረስ ወደ ዛፍ ስር እንጠለል በማለት ሀሳቡን አቀረበ። ሮዝ ቀለም ያላት ቢራቢሮም በመቀጠል " እኔ ጓደኛችን ባቀረበው ሀሳብ እስማማለሁ" በማለት ተናገረች። " አሁን ሳይመጣ ቶሎ እንሂድ" አለች።
ነጯ ቢራቢሮ በመቀጠል ቆይ ግን ለምንድነው ወደ ዛፍ ጋር ወዳለው ሳር የምንሄደው ? በማለት ጠየቀቻቸው። ቢጫዋ ቢራቢሮ " ዝናብ እንዳይመታን ነዋ አለች"። ነጯ ቢራቢሮ እኔ ግን ዝናብ ስለማልፈራ አልጠለልም።"በማለት ነጯ ቢራቢሮ ተናገረች ።
እኔ ፈሪ አይደለሁም በማለት መንገዷን ቀጠለች። ሮዛ እና ቢጫዋ ቢራቢሮዎች ተይ! ተመለሽ እያሏት አልሰማቻቸውም ነበር።ከትንሽ ሰዓታት ብኋላ ዝናቡ አቆመ ሮዝ አና ቢጫዋ ቢራቢሮዎች ነጯን ቢራቢሮ መፈለግ ጀመሩ።
ከብዙ ድካም አና መስላቸት በኋላ ነጯን ቢራቢሮ አገኟት፤ ቢጯዋም ቢራቢሮ ነጯን ቢራቢሮ የት እንደነበርች ጠየቀቻት። ነጯ ቢራቢሮም ከእናንተ እንደራቅሁ በጣም ከባድ ዝናብ እየመጣብኝ እያለ በዚህ አሁን ባገኛችሁኝ ቦታ ላይ ወደኩ አለቻቸዉ።
ነጯም ቢራቢሮ እባካችሁ ጓደኞቼ ይቅርታ አደርጉልኝ በማለት ጠየቀቻቸው። ሮዟ ቢራቢሮ እኛ ይቅርታ እናደርግልሻለን ሌላ ጊዜ ግን የምንባባለዉን አለመስማት ዋጋ እንደሚያስከፊል እወቂ አለቻት።
ነጯ ቢራቢሮ " እሺ ከዚህ በኋላ ቃል እገባላችኋልሁ የምትሉኝን ሁሉ እሰማለሁ" በማለት ቃል ተገባቡ።ከዛም ጊዜ ጀምሮ ሶስቱም ቢራቢሮዎች ይደማመጡ እና ይሰማሙ ጀመር።

