

በድሮ ዘመን አንድ አላዛር የሚባል ልጅ ከቤተሰበቹ ጋር ይኖር ነበር። አላዛር ቡችላ በጣም ይወድ ነበር ። የ 6 ዓመቱ ልደት ጊዜ አባቱ አንድ የምታምር ቡችላ እንደ ስጦታ ሰጠዉ። አላዛርም በጣም ተደስተ፤ አባቱንም አመስገነ ።
አላዛርና ቡችላውም በጣም የሚዋደዱ ጓደኛሞች ሆኑ። ከዕለታት አንድ ቀን የአላዛር ቡችላ በድንገት ከቤት ጠፋ፣ አላዛርም ቡችላውን ከቤት ሲያጣ በጣም ደነግጦ ወደ ዉጪ ሲወጣ ቡችላውን የሆነ ሌባ ይዞት ሲሄድ አየ ። አላዛርም እየሮጠ ቡችላውን ይከተል ጀመር።
አላዛር ሌባውን ሲከተል ፣ሌባው ደግሞ ቡችላውን ይዞ ሲሮጥ ልክ አላዛር የማያውቀው ቦታ ደርሶ ነበረ። ሌባውም ቡችላውን የሆነ ቤት ውስጥ አስገብቶ ዘጋበት ።አላዛርም ቡችላው ያለበትን ቤት ሲያየው በሁለት ቁልፍ ተቆልፎ ነበር።
አላዛርም ከአንድ የዛፍ ጥላ ስር ቁጭ ብሎ ሲያስብ አንድ ሀሳብ መጣለት።በአካባቢው እየተዘዋወረም የብረት መጋዝ መፈለግ ጀመረ።ከአንድ ቤት እንኳክቶም የብረት መጋዝ ጠየቀ፤ ሴቲዮዋም ሰጡት።እየሮጠም ሄዶ ቡችላው ያለበትን ቤት ቁልፉን ሰብሮ ቡችላውንም አገኘ።
ቡችላውና አላዛርም ወደ ቤታቸዉ ሊሄዱ ሲሉ መንገድ ጠፋባቸዉ ።አንድ መንገደኛም አግኝተዉ መንገድ ጠየቁት ። መንገደኛዉም ሰዉዬ ፈረስ ይዞ ስለነበረ አላዛር እና ቡችላዉን ፈረሱን ከጠበቀለት መንገዱን እንደሚያሳያቸዉ ቃል ገባላቸዉ።
አላዛርም በጣም ትሁት ስለነበር ፈርሡን ጠበቀለት ። መንገደኛዉም መንገዱን አሳያቸዉ። ጉዟቸዉንም ቀጠሉ።በመንገዳቸውም በጣም እራባቸው።ከአንድ ቤትም አንኳኩተው ምግብ ጠየቁ ሰዎቹም ደግ ስለነበሩ ምግብ እና ውሀ ሠጧቸው ።
ያንንም ከበሉ በኋላ ወደ ቤታቸው ደረሱ። አላዛርም ቤተሰቦቹን ሲያያቸው በጣም ተደሰተ።ያጋጠማቸውን ነገርም ለቤተሰቦቹ አንድ በአንድ ነገራቸው።
ቤተሰቦቹም ወደፊት እንደዚህ አይነት ነገር ቢያጋጥማቸው ማድረግ ያለባቸዉን ነገር በደንብ አሳረዱት። አላዛርና ቡችላዉም በሰላም ከአላዛር ቤተስቦች ጋር መኖር ጀመሩ።

