የእናት ልፋት
ቢታኒያ ጌታነህ
ቢታኒያ ጌታነህ

ከ5 አመታት በፊት እንድ እናት፣ አባት ና ልጅ ይኖሩ ነበር፡ ከጊዜያት በኋላ አባትዬዉ በጠና ታሞ ሞተ ። በዚህ ጊዜ እናት ና ልጅ ችግር ላይ ወደቁ።እናትየዉ ስራ ልታገኝ አልቻለችም ነበር ። ከእለታት አንድ ቀን አንድ ሰዉዬ አግኝታ ችግሯን በሙሉ ነገረችዉ ። እሱም ደረቅ እንጀራ እንድትሽጥ ሱቅ ሰጣት።

1

እሷም መስራቱን ቀጠለችበት ። ያንን ለፍታ የምታመጣዉን ገንዘብ ለልጄ ለወደፊት ህይወት ብላ እየቀነሰች ታስቀምጥለት ነበር ። ልጁ ግን ገንዘቡን ለምን እንደምታስቀምጠዉ ሳይገባዉ ገንዘቡን ይሰርቅ ነበር። ታዲያ በዚህ ጊዜ እናትየዋ ብሩ ስለሚጣፉበት ግራ ትጋባ ነበር ።

2

አንድ ቀን ልጁ በሰረቀዉ ብር ብስኩት ገዝቶ ሲበላ መምህሩ ያገኙታል። መምህሩም ብሩን ከየት እንዳመጣዉ ጠየቁት ። እሱም እዉነቱን ለመናገር አልፈለገም ነበር። በጥያቄ ሲያስጨንቁት ግን እውነቱን ተናገረ። ያደረገዉ ተገቢ ስላልነበር ሊያስተምረዉ ፈለገ።

3

መምህሩም ወላጅ እንዲያመጣ አደረጉት ። እናቱም ተጠርተዉ መጡ ። በዚህ ጊዜ መምህሩ ሁሉንም ነገር ለእናቱ ነገራቸው ። እናትየዉም ገንዘቡን ማን እንደሚወስድባቸዉ አወቁ ። በዚህ ጊዜ እናትየዉ ልፋታቸዉ መና እንደ ቀረ ተስምቷቸዉ በጣም አዘኑ።

4

ልጁም እናቱ እንዳዘኑበት ሲያዉቅ ጥፋቱን ሁለተኛ ላይደግመዉ ቃል ገባ።

5
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የእናት ልፋት
Author - ቢታኒያ ጌታነህ
Illustration - ቢታኒያ ጌታነህ
Language - Amharic
Level - First paragraphs