

ከዕለታት አንድ ቀን በአንድ አካባቢ የሚኖሩ ታሜ ና ቦቦ የሚባሉ ጓደኛሞች ይኖሩ ነበር።የታሜና የቦቦ ፀባይ በፍፁም የተለያየ ነበር። ቦቦ በጣም አስቸጋሪ ና ቆሻሻ የሚወድ ልጅ ነበር ።
እናቱም ቀን በቀን ትመክረዉ ነበር ።ነገር ግን እናቱንም ሆነ ጓደኛዉን የሌሎችንም ሰዎች ምክር አይሰሙም ነበር።የቦቦ በጣም የሚጠላው ፀባዩ ቆሻሻ መውደዱ ነበር። የቦቦ ጓደኛ ታሜ በቤተሰቦቹም ሆነ በሌሎች ሰዎች ተወዳጅ ነበር።
ታሜ ቦቦን ሁልጊዜ ይመክረዉ ነበር። ቆሾሾ ሲነካ እንደዚህ ይለዋል ቦቦ ተዉ እረፍ! እሱ ነገር ሊያሳምምህ ይችላል ።በሽታም ሊያሲዝህ ይችላል። ለምሳሌ እንደ ጉንፋን፣እንደ ተቀማጥ ፣ ቁርጠት እና ለብዙ በሽታዎች ልትጋለጥ ትችላለህ ።
ይለዋል ነገር ግን እሱ ምንም አይስማዉም ነበር ። የቦቦ ቤተስቦች በጣም ይጨነቁ ነበር ። ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማስብ ጀመሩ። ነገር ግን ምንም ሀሳብ አልመጣላቸዉም። ታሜ በጠዋት ተነስቶ ቁርሱን በልቶ ሲጨርስ ወደ ጥናቱ ገባ ቦቦ መጣና እንጫወት አለዉ።
ነገር ግን ታሜ ፍቃደኛ አልነበረም ቦቦም ተናዶ ለብቻው ለመጫወት ወጣ።ታሜም ቦቦን ጠርቶ ተው! አትጫወት አጥና አንተ ብትጫወት እንኳን ቆሻሻ ላይ ነው አለው።ቦቦም አፉን ይዞ በጣም ሳቀበት። አንደዚህም አለው።"
ታሜ ጓደኛዬ ተው ሞኝ አትሁን" አለው። "ከእኔ ጋር ሄደህ ቆሻሻ ጋር ሄደን ዝንብ ማባረርና መግደል መጫወት ይሻልሀል"አለው። ታሜም እኔ በአንተ ሀሳብ አልስማማም አለው። እና እየሮጠ ወደ ቤቱ ተመለሰ።
ቦቦም እየሮጠ ወደ ጨዋታው ሄደ። ቆሻሻ ላይም ሲንደባለል እና ዝንብ ሲገድል ቆየ። ሲሰለቸውም እያነጠሰ ወደ ቤቱ ሄደ እንደገባም ተኛ። ቤተስቦቹ በጣም ተጨነቁ። ግራም ገባቸዉ ታሜም በንጋቱ መጣ።
በጣም ደነገጠ ቦቦ ታሞ አልጋ ላይ ተኝቶ ነበር።
ታሜም ደንገጥ አለና እናቱን እንዲህ አላት፤ ምን ሆኖ ነበር ቦቦ የታመመዉ አለ፤ የቦቦሞ እናት የእኛን ምክር አልሰማ ብሎ ቆሻሻ ላይ ሲንደባለል ይኸዉ እንዲ ሆኖ ቀረ አሉት፣ ከትንሽ ጊዜያት በኋላ ጓደኛዉ ታሜ እያስታመመዉ ቆየ።
ከዛም ቦቦ ተሻለዉ ከዛም ጓደኛዉን ቤተስቦቹን እና ሌሎችን ሰዎች ጠርቶ ይቅርታ ጠየቀ ከዛም ጓደኛውን ይቅርታ ጠየቀ፣ ጥፋቱንም አመነ። ታሜና ቦቦ የረጅም ጊዜ ጓደኛሞች ሆኑ።
ጥያቄ ልጆች ምን ተማራችሁ?

