ቅን አመለካከት
ታሪኳ መንግስቱ
ታሪኳመንግስቱ ናሆምእና ታሪኳ

በድሮ ዘመን በአንድ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ አንድ ትልቅ አባት ነበሩ።ከጎረቤታቸው ጋር ይኖሩ ነበር። እዛ አካባቢ ይልቅ ሰዎች ቅን አመለካከት ያላቸው እና ደግ ናቸው። እዛ አካባቢ ብዙ ዛፎች አሉ። ከዛ ዛፍ መካከል አንዱ የኢንጆሪ ተክል ነበር።

1

አንድ ቀን ትልቁ አባት የኢንጆሪውን ዛፍ ውሀ ሲያጠጡ የተመለከተ ሰውየ በጣም ተገርሞ ይህንን የኢንጆሪ ተክል መቼ ሊበሉት ነው? እያለ ለራሱ ጥያቄ መፍጠር ጀመረ።ሲያሰላስል የነበረውን ለመጠየቅ ወሰነ።ትልቁ አባትም ምነው ቆምክ ? አሉት።

2

ሰውየው በድጋሜ ለራሱ ጥያቄ ፈጠረ። እኝህ አባት መቼስ ለራሳቸው አይደለም ኢንጆሪ የሚተክሉት አለ። እነዚህ አባት ምን ያህል ቀና አመለካከት እንዳላቸው እየተገረመ ቆሞ ቀረ። ትልቁን አባት ያሰበውን በድፍረት ከጠየቀ በኋላ አባትየው
ልጄ ስማኝ ቀና አመለካከት ምን እንደሆነ ታውቃለህ አሉት?

3

ሰውየውም አዎ አውቃለሁ አላቸው። ቀና አመለካከት ከአወቅህ ይህንን ኢንጆሪ ለቀጣዩ ትውልድ ነው የምንከባከበው። ስለዚህ ልጄ ማንም ሰው ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለቀጣዩ ትውልድ ማሰብ አለበት አሉት። ሰውየውም በትልቁ አባት ቀና አመለካከት ተገርሞ መንገዱን ለመቀጠል አሰበ።

4

ልጁም ያባትየው ምክር እየገረመው መንገዱን ቀጠለ። ማንም ሰው ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለቀጣዩ ትውልድ ማሰብ አለበት ።

5
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ቅን አመለካከት
Author - ታሪኳ መንግስቱ
Illustration - ታሪኳመንግስቱ ናሆምእና ታሪኳ, ታሪኳ መንግስቱ, ናሆም እና ታሪኳ
Language - Amharic
Level - First paragraphs