ሞኙ አይጥ እና ብልሁ ድመት
አላዛር ደበበ
አላዛር ደበበ

ከእለታት አንድ ቀን አንድ ሞኝ አይጥ ነበር፡፡ አንድ ቀን አንድ ቤት ውስጥ ሰተት ብሎ ገባ፤ እዛ ቤት ውስጥ ያሉትን ምግቦች እንክት አድርጎ በላቸው፡፡ የቤቱም ባለቤት ሲመጣ ቤቱ ምስቅልቅል ብሎ ነበር፡፡ ያ አይጥ እዛ ቤት ውስጥ መግባቱን አላቆመም ነበር፡፡

1

የቤቱ ባለቤትም በጣም ተናዶ ስለነበር አንድ ሞኝ ድመት አመጣ ። ያ አይጥ መጣ ነገር ግን እንዳሰበው አልነበረም፡፡ ያንን ድመት እንዳየው በጣም ደንግጦ እየሮጠ ከቤቱ ወጣ፡፡ ያየውን ነገር ስላላመነ ወደ ቤቱ ተመልሶ ገባ። ያ ሞኝ ድመት ግን አላየውም ነበር።

2

የቤቱ ባለቤት ይህንን አይጥ ስላልያዘለት ይህንን ድመት ከቤቱ አስወጥቶ ሌላ ድመት አመጣ። ድመቱም ብልህ ስለነበር ያንን አይጥ መጠበቅ ጀመረ፡፡ ያአይጥ ድመቱ መኖሩን አላረጋገጠም ነበር፡፡ አይጡም እንደለመደው ወደዛ ቤት መሄዱን ተያያዘው፡፡

3

ድመቱም አይጡን ሲጠብቅ በጣም ስለራበው ይህንን አይጥ መያዝ አለብኝ ብሎ በራስ መተማመን ሰፈረበት፡፡ ያአይጥ እየሮጠ ወደ ቤቱ ገባ። ያ ድመት አይጡ መግባቱን አረጋግጦ በሩን ዘጋው። ድመቱም አይጡን ማባረሩን ያዘ፡፡ አይጡንም ያዘው።

4

የቤቱም ባለቤት በዚህ ብልህ ድመት በጣም ተደሰተ፡፡

5
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሞኙ አይጥ እና ብልሁ ድመት
Author - አላዛር ደበበ
Illustration - አላዛር ደበበ
Language - Amharic
Level - First paragraphs