

በድሮ ጊዜ ሁለት እህትማማቾች ነበሩ። ታዲያም የአንደኛዋ ስም ራሄል ሲሆን የሌላኛዋ ስም ደግም ፋጡማ ነበር።ፋጡማ ለወላጆቿ ታዛዥ ፣በትምህርቷ ጎበዝ፣የማትዋሽ እና ታላላቆቿን የምታከብር ልጅ ነች፡፡ በዚህም የተነሳ በአካባቢው ማህበረሰብ ተወዳጅ ልጅ ነበረች፡፡
ራሄል ደግሞ በትምህርቷ ሰነፍ፣ ለወላጆቿ የማትታዘዝ፣ ታላላቆቿን የማታከብር እና ውሸታም ልጅ ናት።እናም ራሄል በአካባቢው ማህበረሰብ ተወዳጅ አልነበረችም። አንድ ቀን የነራሄል እናት '' ራሄል ለእጄ መታጠቢያ የሚሆን ውሀ ከባልዲ ቀድተሽ አምጪ" ብለው አዘዟት።
ራሄልም "እማዬ እጆቼ ይቆሽሻሉ፤ እናም ይበርደኛል" ስትል መለሰችላቸው፡፡የራሄልም እናት በጣም ተበሳጩ፡፡ ፋጡማ የእናቷን መበሳጨት ምክንያት ስላወቀች ወዲያውኑ ለእናቷ ውሀ ቀድታ ሠጠቻቸው እናቷም ፋጡማን እደጊ ብለው መረቋት፡፡ ፋጡማም የእናቷን ምርቃት አሜን ብላ ተቀበለች፡፡
አንድ ቀን መምህራቸው ከ1-3 ለወጣ ተማሪ በአመቱ መጨረሻ ሽልማት እንደ ሚሸልሙ ቃል ገቡላቸው። ፋጡማም ከ1-3 ለመውጣት እያጠናች ነው፡፡ ፋጡማ ራሄልን እንድታጠና ነገረቻት እሷም "አልፈልግም'' አለቻት፡፡ በድጋሜ አጥኒ በማለት ነገረቻት፡፡
ራሄልም "የፈተናው ጊዜ አልተቃረበም ብዙ ጊዜ ስላለን አሁን ሳይሆን ቡኋላ ይሻላል፤ ይልቅ አሁን እንጫወት" ስትል መለሰችላት፡፡ ፈተናውም ደረሰ፤ ፋጡማም አለፈች፤ ሽልማቱንም ተሸለመች፡፡ ራሄል ወደቀች፤ ራሄልም ወላጆቿን፤ መምህሯን እና እህቷን ይቅርታ ጠየቀች።
ከዚያን ጊዜ ቡኋላ ባህሪዋን አስተካከለች።

