ሶስቱ ጓደኛሞች
ሶስና ትዕግስቱ
ትዕግስቱ ታደሠ

ዲና፣ድሩሲል እና ሄቨን በጣም የሚዋደዱ ጓደኛሞች ናቸው። ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ ፣ ከትምህርት ቤት ሲመጡ፣ ሁልጊዜ አንድ ላይ ሆነው ነበር፡፡ ሁልጊዜም አንድ ላይ ነበር የሚታዩት። ዲና ከሁለቱም በእድሜ ትበልጣቸው ነበር፡፡ ከዲናም ብዙ የሚማሩት ነገር ስላለ በጣም ይወዷት ነበር፡፡

1

ዲና እና ድሩሲል አብረው በሚሆኑበት ጊዜ ሄቨን እጅግ በጣም ትናደዳለች፤ አብረው ባየቻቸው ቁጥር የሄቨን አይን ደም ይለብስ ነበር፤ የሄቨን ሀሳብ ዲናንና ድሩሲልን ማጣለት ነበር፤ ከዚያም አንድ ሀሳብ መጣላት ለጓደኞቿም እንዲህ አለቻቸው፡፡

2

"እነ ዲና ቤት እንሂድና ዲና መኝታ ቤት እንጫወት" አለች። እነሡም በሄቨን ሀሣብ ተስማምተው ደስ በሚል ጉዞ በነፋሻማ አካባቢ እየተዝናኑ ሄዱ። ነገር ግን አሁንም ሄቨን ውስጧ ተንኮል እያሠበ ስለነበር ፤ በድንገት ዲና "ግን እኛ ቤት ሄደን ምን ልናደርግ ነው?"አለቻት፡፡

3

ሄቨንም በድንጋጤ ስሜት ፈጠን አለችና "ያዉ እንደተለመደዉ በመጀመሪያ አኩኩሉ እንጫወታለን፡፡ በመቀጠል ተጫውተን ከጨረስን በኋላ ቁጭ ብለን እናወራለን ከዛም እኔ ያንቺን ልብስ ከቁምሳጥንሽ ውስጥ አውጥቼ አይልሻለሁ፡፡ በመጨረሻም ተቃቅፈን እንለያያለን"፡፡አለቻቸው፡፡

4

ከዚያም ዞር ብለ አፌዘችባቸው። ዲናም "በቃ እንሂድ'' ስትልድ ድሩሲልም "እሺ የኔ ውድ ጓደኛ" ስትል ሄቨን በጣም ተናደደችና ንዴቷን ዋጥ አድርጋ ጉዟቸውን ቀጠሉ። ወደ ቤት እንደደረሱም ጨዋታቸውን ጀመሩ።

5

በመጀመሪያዉ ዙር ሄቨን ተደፍታ"አኩኩሉ፣ አኩኩሉ" ስትል እነዲና ደሞ"አልነጋም፣ አልነጋም" ማለቱን ተያያዙት፡፡ በዚያም ጊዜ የሄቨን ድምፅ ጭጭ አለና የዲናን ቁምሳጥን ከፈተችና ለልደቷ የተሠጣትን የፕሪንሰስ ልብስ ቁርጥርጥ አድርጋ ብጫቂ ጨርቅ አስመሰለቻቸው።

6

ከዚያም ድምጿን አለስልሳ "አሁን ድሩሲል ጉዷ ፈላ ለዲና የምትወደውን ልብስ እኛ ከመግባታችን በፊት እንደቀዳደደችው ስነግራት ትጣላላችሁ እናም ዲና አንችን ትታ እኔን ጓደኛ ማድረግ ትጀምራለች'' አለች፡፡ ድምጿን ከፍ አድርጋ "ኧረ ኑ!ኑ!ኑ !የተፈጠረ ችግር አለ ቶሎ ኑ!''

7

በማለት በዘረጋችው ወጥመድ ውስጥ አስገባቻቸው፡፡ ሲመጡም ያዩትን ማመን አቃታቸው ዲና የምትወደውን የፕሪንሰስ ልብስ ተቀዳዶ መሬት ላይ ወድቆ አየችው ከዚያም "ማነው ልብሴን እንዲህ ያደረገው? ማን ነው? ንገሩኝ?" አለቻቸው።

8

ሄቨንም ጣቷን ውድ ድሩሲል እየጠቆመች "እሷ ናት ቅድም ልንገባ ስንል ቀዳዳ የበተነችው" አለች፡፡ ዲናም በጣም ተናደደች በዚያው ቅፅበት ድሩሲልን እየገፈተረች ከቤቷ አስወጥታ በሩን ዘጋችባት፡፡

9

ሄቨንንም "አንቺም ከአጠገቤ ዞር በይ ማንንም ማየት አልፈልግም" ብላ አስወጣ ቻት፡፡ ዲናም በጣም አስተዋይና ብልህ ልጅ ስለነበረች የተረጠረውን ሁሉ ለማስታወስ ሞከረች "እንዴት የምወዳት ጓደኛዬ እኔ በጣም የምወደውን ልብስ ልትቀድብኝ ቻለች?

10

በጣም የምወዳት ጓደኛዬ እኮ ናት፡፡ ሄቨን ደግሞ ብዙ ጊዜ ከድሩሲል በስተጀርባ ስለሷ መጥፎነት ታወራ ነበር ታዲያ እንዴት? "በማለት ማሠብ ጀመረች፡፡በመጨረሻም እውነቱ ሁሉ ተገለጠላት::

11

ይሄ ሁሉ የሄቨን ስራ መሆኑን ስታውቅ ድሩሲልን ይቅርታ መጠየቅ እንዳለበት ተሰማትና ልክ ዘወር ስትል ድሩሲል ስታለቅስ አየቻት ወዲያው ተንበርክካ "ይቅርታ የኔ ውድ ጓደኛ ይቅር በይኝ የተፈጠረዉ ነገር ሁሉ ውሸት ነበር፡፡ የሄቨን ተንኮል ነበር ይቅር በይኝ" አለቻት።

12

ድሩሲልም"እኔ አንቺና እሷን ለማጣላት እንዳይመስልብኝ ነው እንጂ ልብስሽን ስትቀደው አይቻት ነበር፤ ልነግርሽም ስል ድምጿን ከፍ አድርጋ ጠራችሽ እንጂ ልነግርሽ ነበር የኔ ውድ ጓደኛ" አለች ድሩሲል፡፡

13

ከዚያም ዲና''በቃ የኔ ውድ ጓደኛ ያለፈው አልፏል ከዚህ በኋላ ግን እኔ እና አንቺ ብቻ ነን ጓደኛሞች የምንሆነው" አለቻት። ከዚያን ጊዜ በኋላ ሁለቱ በጣም የሚዋደዱ ጓደኛሞች ሆኑ።

14
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሶስቱ ጓደኛሞች
Author - ሶስና ትዕግስቱ
Illustration - ትዕግስቱ ታደሠ, ሶስና ትዕግስቱ, ላምሮት ተሾመ, ኤልዳና በልሁ
Language - Amharic
Level - First paragraphs