ሁለቱ ንጉሶች
ዮናታን ፍሬህይወት
ዮናታን ፍሬህይወት

በድሮ ጊዜ በሁለት ሀገራት የሚኖሩ ሁለት ንጉሶች ነበሩ፡፡ ታዲያ እነዚህ ንጉሶች አንድኛው ንጉስ የሚያስተዳድራቸውን ህዝቦች የሚያስተዳድረው በጭካኔ ነበር። በአንፃሩ ሌላኛው ንጉስ ግን ህዝቡን የሚመራው በፍቅር ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን ሁለቱም ንጉሶች በጠና ታመሙ፡፡

1

ታዲያ ለህመማቸው በፍጥነት መድሀኒት ካላገኙ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚሞቱ ተነገራቸዉ፡፡ መድሀኒቱ ደግሞ የሚገኘው ብዙ መሰናክሎች ካለፉ በኋላ በአንድ በሚያስፈራ ጫካ ውስጥ ነበር፡፡ በዚህ ጉዞ ውስጥ ህይወትን ማጣት ሊኖር ይችላል፡፡

2

የአንደኛው ሀገር ነዋሪዎች በጣም ደነገጡ፡፡ ያ በፍቅር የሚመራን ምርጡ ንጉሳችን ሊሞትብን ነው፤ ብለው አዘኑ፡፡ የሌላኛው ሀገር ህዝቦች ግን ደስ አላቸው፡፡ "በቃ ከዚህ በኋለ ነፃነታችንን ልናገኝ ነዉ"፤ በማለት ጮቤ ረገጡ፡፡

3

የአንደኛው ሀገር ህዝቦች ንጉሳችንን ማዳን አለብን፤ በማለት ሁሉም በአንድነት ምንም አይነት መሠናክል ቢያጋጥመን ተቋቁመን ህይወታችንንም ካጣን አጥተን የተረፍነው መድሀኒቱን ይዘን መምጣት አለብን ብለው ተስማሙ፡፡

4

ጉዞም ጀመሩ። ባሰቡትም መሠረት ብዙ መሰናክሎችን አልፈው መድሀኒቱን ይዘው መጥተው ለንጉሳቸው ሰጡት፡፡ ንጉሳቸውም ዳነ፡፡
እሱም በመደነቅ ከበፊቱ የበለጠ ፍቅር ሰጣቸው፡፡ የሌላኛው ሀገር ንጉስ ግን መድሀኒቱን በፍጥነት ባለማግኘቱ ሞተ፡፡

5

ህዝቦቹም ካለፈው ንጉሳችን በተሻለ በፍቅር ይመራናል ያሉትን ንጉስ መርጠው መኖር ጀመሩ፡፡

6
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሁለቱ ንጉሶች
Author - ዮናታን ፍሬህይወት
Illustration - ዮናታን ፍሬህይወት, ላምሮት ተሾመ
Language - Amharic
Level - First paragraphs