ያፌት እና ዮሀንስ
ኤልዳና በልሁ
ኤልዳና በልሁ

በአንድ ወቅት ሁለት የሚዋደዱ ወንድማማቾች ነበሩ።
እናም ታዲያ ያፌት ጎበዝ፣ ዮሀንስ ሰነፍ ነበሩ። ያፌት የሚወዳቸው እንስሳቶች አሉት። ከትምህርት ቤት እንደመጣ መክሠሡን በልቶ ወደ እንስሳቶቹ ጋር ይሄዳል።

1

ያፌት የቤት ስራውን የሚሰራው ትምህርት ቤት ነው። በየሳምንቱ የግል ንፅህናውንም ይጠብቃል፡፡
እናም ታዲያ ያፌት ብዙ ዶሮዎች አሉት፡፡ ዶሮዎቹ እንቅላል ይጥሉለታል፡፡እንቁላሎቹን ሸጦ የትምህርት ቁሳቁሶችን ይገዛል፡፡

2

ለምሳሌ፦ ደብተር፣እስክርቢቶ፣እርሳስ፣ከለር፣ መፅሀፍ ይገዛል።በዚህም ሥራው ቤተሰቦቹ ያደንቁታል፡፡በተረፈዉ ብር ደግሞ ለእናትና አባቱ ቡናና ስኳር ይገዛላቸዋል። ዮሀንስ ደግሞ በትምህርቱ ሠነፍ ነው።ጥያቄ ሲጠየቅ ግራ ይጋባል፡፡መጫወት፣መብላት፣መተኛት ስራው ነው፡፡

3

ቤተሠቦቹ እቃ እንዲያመጣ ሱቅ ሲልኩት እቃውን አስቀምጦ ይጫወታል፤ እንቅልፋም ነው፤ የግል ንፅህናውንም በወር አንዴ ብቻ ነው የሚጠብቀው እናም ሠውነቱን ያካል፤ ጉንፋን ይይዘዋል።
ከትምህርት ቤት ፎርፎ እግር ኳስ ይጫወታል። ደብተሩን ይቀዳድዳል፡፡

4

አንድ ቀን ፈተና ሊፈተኑ ነበር፡፡ ዮሀንስ ግን የፈተና ሠሞን ምንም አላጠናም፡ በዚህም ጊዜ ፈተና አላለፈም፤ ዮሀንስ ትምህርት ቤት ወላጅ ሳይዝ እንደይገባ ተነገረው።
ዮሀንስም እናቱን ነበር የወሰደው። አስተማሪዎቹም ምን እንደሚያደርግ ዘረዘሩላቸው። ዳግመኛም ወደዛ ነገር እንዳይገባ ቃል አስገቡት፡፡

5

ያፌት የሚለውን መስማት ጀመረ፡፡

6
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ያፌት እና ዮሀንስ
Author - ኤልዳና በልሁ
Illustration - ኤልዳና በልሁ
Language - Amharic
Level - First paragraphs