ማሙሽ ሊስትሮው
Tesfamichael Hailu
Tesfamichael Hailu

በድሮ ጊዜ አንድ ማሙሽ የሚባል የአስራአምስት አመት ልጅ ነበር ።

ማሙሽ የደከሙና በህመም የሚሰቃዩ ቤተሰቦቹን ለመደገፍ ገና በልጅነቱ ነበር ሊስትሮ ስራ የጀመረው ፣ እናም እየሰራ በሚያገኘው ገንዘብ ቤተሰቦቹን ይረዳል።

1

ነገር ግን ማሙሽ የሊስትሮ ስራውን ሲሰራ ቆይቶ ወደቤቱ ሲመለስ ፣ ሌቦች በተደጋጋሚ ለፍቶ ያጠራቀማትን ገንዘብ ይወስዱበት ነበር ።

2

የሰፈሩ ህፃናትም በተደጋጋሚ ከረሜላና ብስኩት እንዲገዛላቸው ያስቸግሩት እና ይመቱት ነበር ።

በዚህም ምክንያት ክፉኛ እያዘነ እና እያለቀሰ ይኖር ነበር ።

3

ከእለታት አንድ ቀን ግን ማሙሽ የቤተሰቦቹ ችግር ላይ መውደቅና መታመም ፣ ሰላም ስለአሳጣው ቤተሰቡን መርዳትም ስለሚፈልግ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ይሄድና በተደጋጋሚ የደረሰበትን ችግር ይናገራል ።

4

ፖሊሶቹም ማሙሽ በነገራቸው መሰረት ሌቦቹን ተከታትለው ይይዟቸዋል ።
ሰፈር እየጠበቁ ከረሜላና ብስኩት ግዛ እያሉ የሚመቱትንም ልጆች የተቸገረን ሰው ፡ መርዳት እንጂ መማታትና ማስቸገር እንደሌለባቸው ፣ እንዲሁም ያላቸውን በማካፈል ፣ ስራ በሚሰራበት ጊዜ ማገዝና በትምህርት መደገፍ መልካም ተግባር መሆኑን ይመክሩዋቸዋል ።

5

ልጆቹም የፖሊሶቹን ምክር ተቀብለው በትርፍ ጊዜያቸው ማሙሽን በማገዝ ጥሩነትና መተሳሰብ ያለበትን ጓደኝነት ፈጠሩ።

6
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ማሙሽ ሊስትሮው
Author - Tesfamichael Hailu
Illustration - Tesfamichael Hailu
Language - Amharic
Level - Longer paragraphs