

የቆሎ ተማሪ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ውስጥ አንድ አገልጋይ በመንፈሳዊ እውቀት እና ምግባር በሚታነፅበት ጊዜ የሚሰጠው ስያሜ ሲሆን አንድ የቆሎ ተማሪ ከድቁና፣ ቅስና እና ሌሎች መንፈሳዊ ትምህርቶችን ብሎም ማዕረጎችን ያገኛል ማለት ነው ።
በድሮ ጊዜ አንድ አካባቢ ላይ ይኖር የነበረ ፣ ዳዊት የሚባል የአብነት ወይም በተለምዶው የቆሎ ተማሪ ነበር።
በአብዛኛው የሀገራችን ክፍል አነዚህ የአብነት ተማሪዎች ፣ከሚኖሩበት ቀዬ ርቀው ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱና ምጽዋትን ከምዕመናን እየጠየቁ ስለሆነ የሚማሩት የተለያዩ ፈተናዎች ያጋጥማቸዋል። እናም ዳዊትና ጓደኞቹ መንፈሳዊ ትምህርታቸውን እየተማሩ ፣ስንቃቸው ስለሚያልቅ በየመንደሩ እየተዟዟሩ ምጽዋት መጠየቃቸው ግድ ነበር ።
ከእለታት አንድ ቀን ዳዊት ከጓደኞቹ ተነጥሎ በዚያ በሚማሩበት መንደር እየለመነ ሳለ ወደ አንድኛው ጊቢ ሲገባ ባለቤቶችሁ እረስተው ያላሰሩት ሀይለኛ ውሻ ይገጥመዋል....
ከዚያም ውሻ ክፉኛ እየጮኸ ሲያሯሩጠው
ጓደኞቹ ያሉበት ቦታ ጋር ይደርሳል ፣ በጋራ ሆነው ውሻውን ከአባረሩ በኋላ ከየትኛው ጊቢ እንደወጣና እዛ ጊቢ በተደጋጋሚ የቆሎ ተማሪዎች ሲሄዱ ውሻ ተረስቶ ሳይታሰር እንደሚያጋጥማቸው ለመምህራቸው ይናገራሉ ።
መምህራቸውም የቆሎ ተማሪዎቹን ሰብስበው በየሰው ቤት የተለያየ ፈተናና ችግር ሊገጥም ስለሚችል ፣ ልጆች ጥንቃቄ እንዲያደርጉና ከየጓደኞቻቸው ጋር መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ይመክሯቸዋል።
እንዲሁም ለህብረተሰቡ ስለአብነት ትምህርት ምንነትና አስፈላጊነት በማስተማር ልጆችን ማገዝ ፤ ያላቸውን ማካፈል መልካምና የተቀደሰ ተግባር እንደሆነ ተናገሩ። ማህበረሰቡም የተማረውን በመተግበር በየአካባቢው የሚመጡ የቆሎ ተማሪዎችን ማገዝ ጀመሩ።
ማህበረሰቡም የተማሩትን በመተግበር በየአካባቢው የሚመጡ የቆሎ ተማሪዎችን ማገዝ ጀመሩ። ዳዊትና ጓደኞቹም ደስ አላቸው ።

