ውሃ እና ኳስ
አቤል አማረ
ቃልኪዳን ጥበበ

ከለታት አንድ ቀን የምወደውን ኳስ ይዤ ከቤት ወጥቼ ጓደኞቼ ጠርቼ ከአባጋሪ ወንዝ አጠገብ ካለው ሜዳ ጨዋታችንን ጀመርን።

1

ከዛ በድንገት የማይታመን ነገር ተከሰተ ምን መሰላችው የምወዳት ኳስ ወንዝ ውስጥ ገባቾ ደግነቱ ግን በጋ ስለነበር ወንዙ አልሞላም።

2

ስለዚያ ወንዙ አይንቀሳቀስም ። ከዚያ እኛ ስለደነገጥን ግማሻችን በድልድይ ተሻግረን ሄድን እኔና 1ድኛው ጓደኛዬ በዚያ ቀረን እኔ አለመሙላቱን ባየ ጊዜ ድንጋይ እየረገጥኩ ለማውጣት ወሰንኩ።

3

የመጀመርያው ድንጋይ እንደረገጥኩ ወደኩ ድንጋይ መስሌኝ ለካ ፌስታል ነው የረገጥኩት ጓደኞቼ ለማውጣት ሲመጡ ከለከልኳቸዉ ለምን እንደሆነ ታቃላችው

4

ለማውጣት ብለው እነሱ እንዳይገብ ነው። ከዛ ሳር እየሳብክ ወጣሁ።

5

የእናቴ ጓደኛ ገላዬን አጠበችኝ

6

እናቴ ስለማታውቅ የእናቴ ጓደኛ ወደ ቤት ይዛኝ ሄደች ለእናቴ ነገርኳት ከዚያ እናቴ እዚያ ሰፈር እንዳልጫወት ነገረችኝ እኔም ተቀበልኳት።

7
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ውሃ እና ኳስ
Author - አቤል አማረ
Illustration - ቃልኪዳን ጥበበ
Language - Amharic
Level - First paragraphs