

በአንድ ትምህርትቤት ዉስጥ በጣም የሚዋደዱ ጓደኛሞች አቤሜሊክ እና ባርኮት የ ስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ነበሩ።አቤሜሊክ ጎበዝ ሲሆን ባርኮት ግን ደካማ ነበር።እናም ሰአቱን በአግባቡ አይጠቀምም አቤሜሊክ ግን ሰአቱን በአግባቡ ከፋፍሎ ይጠቀማል ።
አቤሜሊክ በእረፍት ስአት ሲያጠና ጓደኛዬ ባርኮት እናጥና ብሎ ሲጠይቀው ሁልጊዜ የባርኮት መልስ በኋላ እቤት አጠናለሁ ብሎ ወደ ጨዋታ ነዉ ። ከዚያም የአንደኛ መንፈቅ አመት ማጠቃለያ ፈተና ደርሶ አቤሜሊክ ሲያጠና ባርኮት ግን ያው እንደለመደው ጨዋታ ላይ ነበር።
እንዲህ እንዲህ እያለ ፈተናው ደረሰ ከዚያም ባርኮት ፈተናው በጣም ከበደው እንዳጋጣሚ ሆኖ ከአቤሜሊክ ጋር አብረው ነበር የተቀመጠው። ከዚያም ባርኮት ከአቤሜሊክ እያየ ሰራ አቤሜሊክ ተው ቢለውም ምን ችግር የለውም እያለ ሰራ።ፈተናው ታርሞ ሲሰጣቸው መምህሮቹ ግራ ተጋቡ ምክንያቱም ባርኮት ሰነፍ እንደሆነ ነበረ የሚያውቁት ።ግን ውጤቱ ጥሩ መጣ።
መምህሩ ግራ በመጋባት እውነት ባርኮት ይህ ያንተ ውጤት ነው ብሎ ጠየቀው ?ባርኮትም እየዋሸ እና እየተንተባተበ አዎ ቲቸር በማለት መለሰለት። መምህሩ ባያምንበትም እንኳን ጎበዝ ባርኮት በዚሁ ቀጥል ብሎ አበረታታው።
ባርኮት ጥሩ ውጤት ስላመጣ ደስ ብሎት ለወለጆቹ አሳያቸው ። ወላጆቹም በውጤቱ ተደሰቱ ከዚያም በኋላ ቤተሰቦቹም ሆነ መምህሮቹ ጎበዝ አድርገው ማሰብ ጀመሩ።
የሁሉንም ተማሪዎች ትክክለኛ ዉጤት የሚያሳይ ሊፈተኑ ወራቶች ሲቀራቸው ተማሪዎች ቤተመጻሕፍት አንዳንዶቹ ደግሞ የዛፍ ጥላ ስር ሆነው ሲያጠኑ ሲረዳዱ ይውሉ ነበር።ባርኮት ግን ያው ኩረጃን ተማምኖ ከህጻናት ጋር በየመንገዱ ኳስ መጫወት ጊዜው ሄደ።ፈተናው ሲደርስ ሁሉም ስላጠኑ አልተጨናነቁም ነበር ።ባርኮት ግን ከአቤሜሊክ ጋር ባልቀመጥስ እያለ ይጨነቃል ።
ባርኮት እንደፈራው ተማሪዎቹ በአልፋቤት ተቀመጡ ።አቤሜሊክ በA ረድፍ ባርኮት ደግሞ በB ረድፍ ተቀመጡ።ባርኮት ደንግጦ ወይኔ ጉዴ አለ።ሊኮርጅ ቢንጠራራም ማንም ሊያሳየው አልቻለም።ጨርሰው ሲወጡ ባርኮት አለቀሰ።ጓደኞቹ ምን ሆነህ ነው ሲሉት ፈተናው ከብዶኝ አላቸው ሳቁበት አየህ አጥና ስንልህ ሳታጠና ምን ጠብሸህ ነበር አሉት።ከትንሽ ወራት በኋላ ታርሞ ውጤታቸው መጣ።
ውጤታቸውን እያዩ ተደሰቱ ሁለት ልጆች እና ባርኮት ግን ከፍቷቸው ነበር ።ምክንያቱም አላለፋም ነበር ።አቤሜሊክ እና ሌሎች ጓደኞቹ አዘኑበት።የኩረጃ መጀረሻው ይህ ነዉ አሉት።
ወደ ቤት ስሄድ ደግሞ ቤተሰቦቹ በጣም አዘኑበት።እሱም በራሱ በጣም አዘነ።
እና ልጆች ከዚህ በላይ እራስን መግደል አለ ። ኩረጃን መቀነስ ከቻልን ማጥፋት የእኛ ሀላፊነት ነው ።ካስኮረጅን ገዳይ ከኮረጅን ደግሞ ልክ እንደ ባርኮት ሟች ሆንን ማለት ነው ።

