

በአንድ አነስተኛ ከተማ ዉስጥ አንድ ዳዊት የሚባል የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ነበር የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ ዝግጅት አጠናቀቀ ትምህርት ቤት እንደደረሰ መምህርአቸዉ ወደ ክፍል ገብተዉ ለቀጣይ ቀን የቤት ስራ ተሠጣቸው። የቤት ስራቸው ደግሞ ወላጆቻቸውን የሚወዱትን ፍራፍሬ ጽፈው እንዲመጠሐ አዘዘቻቸው።
ዳዊት ከትምህርት ቤት እንደተመለሰ ቦርሳው ከጀርባው ላይ አዉርዶ ወደ አባቱ ሄዶ እንዲህ አለዉ አባዬአለ አባቱም ዉይ መተሀል እንዴ አለዉ።ዳዊት መምምህራችን ቤተሰቦቻችሁ የሚወዱትን የፍራፍሬ አይነት ጽፋችሁ አንጡ ተብለናል አለው ።
የዳዊት አባት እንህ አለዉ።እኔ የምወደው ፍራፍሬ ሙዝ ነዉ አለው።የሙዝ ጠቀሜታ ደግሞ ሆዳችንን ሲያመን ብንመገብ ይሻለናል አለዉ።ዳዊትም አባቱን አመስግኖ ወደ እናቱ ጋር አመራ።
ዳዊት እናቱም ጋር ሄዶ እናቱ የምትወደው ፍራፍሬ ጠየቃት እናቱም በጣም የምወደዉ ፍራፍሬ ሀባብ ነው።አለችው የሀባብ ጥቅም ደግሞ ኩላሊትን ንጹሕ ለማድረግ ነዉአለችዉ ።
እናቱ ለዳዊት አልሚነት ያለው ምግብ ምን እንደሆነ ጠየቀችዉ እሱም እንደማያውቅ ነገራት።አልሚነት ያለዉ ምግብ ማለት ለሰዉነት ግንባታየሚሰጥ ነዉ አለችዉ።ከነሡም መካከል ካርቦሀይድሬትና ፋት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።ካርቦሀይ ድሬት የሚሰጠው ጥቅም ሀይል ይሠጠናል።ግብአቱ ደግሞ ዳቦ፣በቆሎ ወዘተ ናቸዉ።ፋትሚሠጠን ደግሞ ግብአት የእንስሳት ተዋጾ ናቸዉ።ዳዊትም እናቱን አመስግኖ ሄደ።
በቀጣዩ ቀን ዳዊት ወደ ትምህርት ቤት ሄዶ ለጓደኞቹ ማንበብ ጀመረ ። ከዛም መምህራቸው ወደ ክፍል ገብታ የሰጠቻቸውን የቤት ስራ መልስ እንዲሰጣት ጠየቀች። ዳዊትም እጁን አውጥቶ ቤተሰቦቹ ስለነገሩት ነገር ዘርዝሮ ለመምህሩና ለተማሪዎቹ አነበበላቸው ። መምህሯም በጣም ተደስታ ጎበዝ ዳዊት አለችዉ።ሁላችንም ፍራፍሬ መመገብ አለብን አለ ።

