

በድሮ ግዜ አንድ ብልህ ሰው ነበር ።ይህ ብልህ ሰው ታማኝ ሰው አክባሪ ተወዳጅ ሰው ነበር ።
ከለታት አንድ ቀን ብልሁ ሰው ዘመዶቹን ለመጠየቅ አሰበ።እናም ወደ ዘመዶቹ መንገድ ቀጠለ ።የዘመዶቹ ቤት እሩቅ ስለነበር ከጠዋት የጀመረው ጉዞ እስከ ማታ ቀጠለ ።
ጸሀይዋ ልትጠልቅ አካባቢ ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ባለበት አካባቢ ደረሰ። ጫካውን አቋርጦ ለመሄድ ወደጫካው ሊገባ ሲል ያልጠበቀውን ነገር ተመለከተ። በጫካው ውሥጥ ባለው መተላለፊያ ላይ ነብሩ በሞተች አይጥ ሢጫወት ተመለከተ።
ግራ ገብቶት ማሠብ ጀመረ። ወደ ኋላ ለመመለስ ቢሞክር ጊዜው እንመሸ ተረዳ። ወደ ቀኝ እና ግራው ሲመለከት ደግሞ አቋራጭ መንገድ የለም። ምን እንደነሚያደርግ ግራ ገብቶት ሳር ላይ ተኝቶ ማሠብ ጀመረ። አንድ ሀሳብ ብልጭ አለለት።
እናም ነብሩ ሳያየው ቀስብሎ ድቡልቡል ድንጋይ መፈለግ ጀመረ። ካገኘ በኋላ አንድ ትልቅ ዛፍ ስር ተደበቀ። ነብሩ እንዳላየው ካረጋገጠ በኋላ ድቡልቡልሏን ድንጋይ ቀስ ብሎ ወረወራት። ድንጋይዋ ከነብሩ ኋላ አረፈች። ነብሩ ደንግጦ ከየት እንደተወረወረ ለማየት ግራ ቀኙን ተመለከተ። ምንም ነገር ማየት አልቻለም
ጠግቦ ስለነበር አይጧን ትቷት የጫካውን መንገድ ይዞ ወደፊቱ መጓዝ ጀመረ። ሰውየውም ከተደበቀበት ወጥቶ በቅርብ ርቀት
ላይሆኖ ነብሩን እየተከተለ መጓዝ ጀመረ። በመጨረሻም ነብሩ የጫካውን መንገድ ትቶወደ ዋሻ ውስጥ ገባ።
ሰውየውም ነብሩ ዋሻውስጥ መግባቱን ካረጋገጠ በኋላ መንገዱን ይዞ በመሄድ ከጫካው ውስጥ ወጣ። አሁን ዘመዶቹ ሰፈር ለመድረስ በቅርብ ርቀትላይ መሆኑን ሲመለከት ፈጣሪውን አመሰገነ።
ጥቂት ከተጓዘ በኋላ ዘመዶቹ ቤት ደረሰ። ዘመዶቹም በጥሩ የእንግዳ አቀባበል ስርአት ተቀበሉት። ብልሁ ሰውም በመንገድ ላይ ያጋጠመውን ነገር በሙሉ ነገራቸው። እነርሱም በመገረም ሲያዳምጡት ከቆዩ በሆላ በጣም ብልህ ሰው ነህ ሲሉ ገለጹት።

