ዳክዬዋና አዞው
ዳናዊት ሽፈራው
ዳናዊት ሽፈራው

ዳክዬዋ በዉኃ ውስጥ እየዋኘች ነበር። በጣም ደስ ብሏታል። ከኋላዋ ደግሞ ትልቅ አዞ እየመጣባት ነበር። ታየው ይሆን?

1

ዳክዬዋ በደስታ እየዋኘች ነው። የተመለከተችው ግን አይመስልም። ግን የሆነ ነገር እየጠረጠረች ነው። ድንገት ዘወር ብላ ስትመለከት አዞውን ተመለከተችው። በጣም ፈራች።

2

ለማምለጥ ሞከረች። ግን በጣም ለመፍጠን አልቻለችም። ዉኃው እያሰመጣት መጣ። እንደምንም ለማምለጥ መንሳፈፍ ጀመረች።

3

እንደምንም አመለጠች። አውሬውን ያመለጠች ቢመስላትም አውሬው ግን ተደብቆ ነበር። አብሯት እየተከተላት ነበር። እሷም መጓዟን ቀጠለች።

4

አውሬውም እየተከተላት ነበር። ድንገት ወጥቶ ለመያዝ ሲሞክር በጣም ኃይለኛ ዉኃ መጥቶ ዳክዬዋን ወሰዳት።

5

ዉኃውም በጣም ሩቅ ቦታ ወስዷት በጣም ደክሟት ስለነበር ከዉኃው በመውጣት ዳርቻው ላይ አረፍ አለች።

6

ዳክዬዋም አረፍ እንዳለች የሷ ዓይነት ብዙ ዳክዬዎች አገኘች። በጣም ደስ አላት።

7
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ዳክዬዋና አዞው
Author - ዳናዊት ሽፈራው
Illustration - ዳናዊት ሽፈራው
Language - Amharic
Level - First paragraphs