አይጡና ወንድሜ
ተዋበች ተገኝ
ተዋበች ተገኝ

ከእለታት አንድቀን አንድበቀለ የተባለ ልጅ ነበረ እህቱ ብርቱካን ትባል ነበር እናታቸው ቤት አስተካክሉ ብላ ስትሄድ ብርቱካን ቤት ለማስተካከል መጥረጊያ በያዘችበት ጌዜ ከአልጋ ስር አይጧ ወጥታ በወንድሟ እግርስር ሄደች እሱም እየዘለለ ልብሱን ይዞ ወጣ።

1

በዚያን ጊዜ እናታቸው ከገብያ መጣች ምን ሆነህ ነው የወጣህው ስትለው ውጣ ብላኝ ነው ብሎ አሳበበ ከዜያም እናቱ እህቱን ምን አርጎሽ ነው ውጣ ያልሽው ስትል ጠየቀቻት አይጧ መታበት ነው እንጂ ውጣ አላልኩትም አለች።

2

አንተ ውሸታም ለምን ትዋሻለህ ስትል ለመምከር ምከረች ምክሯንም ሁለተኛ አንደማይደግም ነገራት እሷም ተደሰተች እሰይ ልጄ ምክሬን ሰማኝ ሰትል ፈጣሪዋን አመሰገነች።

3

አንድ ቀን እሱቅ ተልኮ ደርሶ ሲመለስ አይጧ ከድንጋይ ስር ብቅ አለችበት እየጮሀ እሮጠ ከዚያም ምነው ማን መታህ ስትል እናቱ ጠየቀችው አይጧ አይጧ አያለ መሮጡን ቀጠለ

4
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አይጡና ወንድሜ
Author - ተዋበች ተገኝ
Illustration - ተዋበች ተገኝ
Language - Amharic
Level - First paragraphs