

ባንድ አካባቢ የሚኖሩ ባህላችንና ወጋችንን በማቀናጀት ዳኝነትን በሸንጎ ዋርካዎች ስር የሚሰጡ ወይም የሚዳኙ አቶ አንዳርጌ
የተባሉ አባት ነበሩ ሁሉም ፍትህ ፈልጎ ወደ እሳቸው ሄዶ ሳይስማማ የተመለሰ የለም።
ከእለታት በአንድ ቀን የአቶ አንዳርጌ ባለቤት ከጎረቤታቸው ተጣልተው ወደባለቤታቸው ማለትም ወደዳኛው ዘንድ ሄዱ።ዳኛውም እንዳዩዋቸው በጣም ደነገጡ ግን ሁለቱንም በእኩል መዳኘት እንዳለባቸው ወሰኑዳኛው ባለቤታቸውን ከሳሽ ተከሳሽ ምን እንዳጠፉ ይንገሩኝ አሉዳኛው።
ከዛ ከሳሽም ወገባቸውን ያዝ በማረግ እንደዚህ አሉ ያው እንግዲህ በሰፈሩ የታወቀ ምግብ ቤት እንዳለኝ "አገርያወቀው ጸሀይ የምቀው" ነገርነው አንተም ታውቃለህ እናም ሰዋችእኔ የምሰራቸውን ምግብ በውድ ይገዛሉ።
እሷ ግን እኔ ምግብ ሥሠራ ዳቦገዝታ እያሸተተች ዳቦአጣጥማ በልታለች እና ትክፈለኝ ትካሠኝ ነው የምለው አለች በኩራት ዳኛውም ሳቅ በማለት ተከሳሽ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይላሉ አሉ
ዳኛዉ።
ተከሳሽ እኔ የእራሷን ምግብ ለመግዛት በቂ ገንዘብ ስለሌለኝ ባለኝ ሳንቲም ዳቦ ገዝቼ ምግቧን እያሸተትኩ በልቻለሁ። አዎ ግን እኔ ምግቧን ባሸተው ችግሩ ለሷ ኪሳራው ምንድነው አሉ ተከሳሽ።
ዳኛውም ወደ እሩቅ ትክዝ ብለው ሲመለከቱ የሀገራቸው በጣም ሀብታም የተባለ ሰውዬ በዛ ሢያልፍ አዩ እናም በእረኞች አስጠሩት። ሲመጣም ዳኛው በጆሮው አንዲህ ብለው ነገሩት ። እባክህ ልጄ ያሉህን ሳንቲሞች ከኪስህ አውጥተህ ያዛቸው አሉት። እሱም እንዳሉት አደረገ።
ዳኛው እስቲ ወደ እዚህ የመጣችሁበትን አስረዱኝ። እነሱም በተራ በተራ ነገሩት። እሱም እንደ እሱ ከሆነ የዝችን ሴትዮ ሂሳብ እኔ ልከፈል አለ። ከሳሽ ተስማማች እናም እንዲህ አለች። "የት ፍጭው ዱቄቱን አምጭው" አለች።
ባለ ሀብቱም የያዛቸውን ብዙ የወርቅ ሳንቲሞች ኮሽ ኮሽ ሲያረጋቸው ሴትየዋ በጣም ደስ አላት። ግን ሰውየው ሳንቲሞቹን ወደ ኪሱ ከተታቸው ዳኛውም አመሰግናለሁ።ልጄ አሉት።እሱም መንገደን ቀጠለ።ሴትየዋም የታለ የታለ የከፈለኝ አለች።
ዳኛውም አየሽ አንቺ ስላሸተተች ከሰስሻት እሷም ባለ ሀብቱ ሳንቲም አንኮሻኩሾ ከፈለሽ ስለዚህ ሰውን ባልሆነ ነገር አትወንጅሊ ሰውን ለመጉዳት አታስቢ አሏት።
ከሳሽም ተከሳሽ እግር ላይ ወድቃ እባክሽ ይቅር በይኝ አለቻት።እሷም ተነሽ ተነሽ ይቅር ብዬሻለሁ።ዋናው አንቺ ከስተትሽ መማርሽ ነው አለቻት።
ዳኛውም አያችሁ ጸባችሁ አይበጃችሁም የሚበጃችሁ አንድነታችሁ ነው።ብለው አስታርቀው ሸኟቸው።

