ሁለቱ ወንድማማቾች
ዮሀንስ ተስፋየ
ዮሀንስ ተስፋየ

ትልቁ አበበ ይባላል።
ትንሹ ደግሞ ከበደ ነው።

1

ሁለቱም ልደታቸውን አብረው ነው የሚያከብሩት። ምክንያቱም አበበ በተወለደ ልክ በሁለት አመቱ ነው ከበደ የተወለደው። ስለዚህ ሁለት አመት ይበልጠዋል አበበ ከበደን።

2

አበበና ከበደ በልደታቸው ቀን ይጣላሉ።

3

ምክንያቱም አበበ ትልቅ ስለሆነ ከከበደ የተሻለ ስጦታ ስለሚሰጠው ነው።

4

ከበደ ደግሞ አበበን አካፍለኝ ስለሚለው አበበ ደግሞ አላካፍልም በማለት ይጣላሉ።

5

እነዚህን ልጆች ሲያዩ የሚገረሙ አንድ ጎረቤት ሽማግሌ ነበሩ።

6

አንድ ቀን ጠሯቸውና ሰብስበው መከሯቸው። መዋደድ እንዳለባቸውና ያላቸውን በጋራ መጠቀም እንዳለባቸው መከሩአቸው።

7

እነሱም ከዚያን ቀን ቡኋላ ተስማሙና በጋራ መጠቀም ጀመሩ። ከዚያም ተሳስቀው በደስታ ተቃቀፉ።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሁለቱ ወንድማማቾች
Author - ዮሀንስ ተስፋየ
Illustration - ዮሀንስ ተስፋየ
Language - Amharic
Level - First paragraphs