ምክሩ
ኤልዳና በላይ
ኤልዳና በላይ

ከእለታት አንድ ቀን አንድ ሰውዬ ከስራ ደክሞት እየተመለሰ እያለ አንዲት ሴትዮ ያገኙታል ከዛም ልጄ እንዴት ዋልክ አሉት። ደህና ምን ልርዳዎት እማማ ይላቸዋል።ከመስሪያ ቤትሰርተህ የመጣኸውን ብር ስጠኝናየገንዘብክን ምክር ያክል ልምከርክ በጣም ይጠቅምሀል አሉት።እሱም ሰርቶ የመጣው2000 ብር ነበር።ከዛም እሺ ብሎ ይሰጣቸዋል።

1

ከዛም በመቀጠል ሁለት ምክር ልምከርክ አሉት። እሱም እሺ ብሎ ለመስማት ተዘጋጀ። እሳቸውም ምክራቸውን ቀጠሉ አንደኛው ምክሬ ተስፋ አትቁረጥ ሁለተኛው ምክሬ ደግሞ ትእግስተኛ ሁን።አደራ ልጄ ይህንን ምክሬን ተግባራዊ አድርግ ይጠቅምሀል ብለው ተለያዩ።

2

ከዛም መንገዱን ቀጠለ ። መስሪያ ቤቱ ከቤቱ ትንሽ ራቅ ይላልና መንገዱን ቢሄድ ቢድ አላልቅ ይለዋል። እግሩንም ቀስ በቀስ ማንቀሳቀስ ያቅተዋል። ከዛም ትንሽ አረፍ ልበል ብሎ ቁጭ ሊል ሲል እማማ ተስፋ አትቁረጥ ያሉት ነገር ትዝ ይለዋል።ከዛም ቃላቸው ትዝ ሲለው ራሱን አበርትቶ መንገዱን ቀጠለ።

3

ከዛም እንደ ምንም ቤቱ ደረሰ። ከዛም ሚስትየው ምሳ አቅርባ እየበሉ እያለ የሰራኸው ብር የታለ አለችው?ከዛም የሆነውን ሁሉ ነገራት።እሷ ደግሞ በጣም ተናዳ ለምን እንደዚህ ሆነ ብላ ትጨቃጨቃላችሁ።እሱም ተናዶ ሊደበድባት ሲል ሴትዬዋ ትእግስተኛ ሁን ያሉት ነገር ትዝ ይለዋል።ከዛም ሀሳቡን ሰብስቦ ምግቡን መብላት ቀጠለ።

4

በሌላኛው ቀን ደግሞ ወደ መስሪያ ቤቱ ሄደና ስራውን ጀመረ። ስራውንም እየሰራ እያለ በጣም ደከመውና ሊያርፍ ፈለገ ግን ስራውን ቶሎ መጨረስ አለበት። ሴትየዋ የመከሩት ምክር ትዝ አለው።ከዛም ስራውን በብርታት ቀጠለ።ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ይህ ተፈጠረ።

5

የመስሪያ ቤቱ ሀላፊ መጣና ስራህን አድንቄልሀለሁ። ጎበዝ ብሎ 10000 ብር ሰጠው። እሱም በመደሰት ሰውየውን አመስግኖ ፈጣሪውንና ሴትየዋንም አመስግኖ ወደ ቤቱ ይህንን ዜና ለሚስቱ ሊነግራት በደስታ ወደ ቤቱ ሄደ።

6

በመቀጠል ም ቤቱ እንደደረሰ ለሚስቱ የሆነውን ሁሉ ነገራት። የሴትየዋን ምክር በመስማቱ መጠቀሙን ስለ መስሪያ ቤቱ ሀላፊ ስለሁሉም ነገራት። እነሱም በደስታ ተቃቀፉ። ከዚያም ሕይወታቸውን በፍቅርና በሰላም መኖር ጀመሩ።

7
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ምክሩ
Author - ኤልዳና በላይ
Illustration - ኤልዳና በላይ
Language - Amharic
Level - First paragraphs