3ቱ ጓደኛሞች
በጽናት ዘነበ
በጽናት ዘነበ

ከእለታት አንድ ቀን 3 ጓደኛሞች በአንድ ቤት ውስጥ ይኖሩ ነበር ።አንድ ቀን ወደ ቤታቸው እየሄዱ እያለ አንድ ልጅ ብቻዋን ቁጭ ብላ አዩአት።እነሱም በጣም ስላሳዘነቻቸው ጓደኛሞች እንሁን አሏት ።

1

ከዛም አብረው ወደ ቤታቸው ሄዱ።በዛን ስአት ያቺ ከመንገድ ላይ ያገኟት ልጅ በእነሱ ፍቅር በጣም ስለቀናች እነሱን ማጣላት የፈለገች ።ከዛም አንደኛዋ ጓደኛቸው ጋር ሄደች ።

2

እንዲህም አለቻት ጓደኞችሽ እኮ ከሷ ጋር ተጣልተን አንድ ላይ እንሁን ሲሉ ሰማሁና ልነግርሽ መጣሁ አለቻት።ጓደኛቸው በጣም በመናደድ እሮጣ ወደ ቤታቸው ሄደች።

3

በድጋሚ 2ተኛዋ ጓደኛቸው ጋር በመሄድ ጓደኞችሽ በጣም እንደሚጠሉሽ ሲያወሩ ሰምቼ ልነግርሽ መጣሁ አለቻት ።

4

በመቀጠል 3ተኛዋ ጓደኛቸው ጋር በመሄድ ጓደኞች አንቺን ትተዉ ሌላ የሚያምር ቦታ እንሂድ ሲሉ ሰምቼ ልነግርሽ መጣሁ አለቻት ።

5

በዛን ሰዓት ወደ ቤታቸው መሄዱ ማንም ስላልነበረ ያሰረቻቸውን ጓደኛቸውን በጣም ብዙ ሰአት ጠበቋት ግን አልመጣችም።

6

በዛን ሰአት እሷ እንዳጣላቻቸው አወቁ።ከዛም ቀን ጀምሮ በሰላም እና በፍቅር መኖር ቀጠሉ።

7
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
3ቱ ጓደኛሞች
Author - በጽናት ዘነበ
Illustration - በጽናት ዘነበ
Language - Amharic
Level - First paragraphs