

በድሮጊዜ አንድገጠራማ አካባባ በልመናየሚተዳደሩ ሁለትባልናሚስት ነበሩ።ለራሳቸውተርፈው ለልጆቻቸው የሚሰጡት ምግብ አልነበረም።በዚህ ሁኔታብዙአመታትን ከኖሩ በኋላ ሁለተኛ ልጃቸውንሞትነጠቃቸው። ከቤትውስጥ አንድልጅ እንደቀረባዩጊዜ ልባቸውተነካ። አቅማቸውሲደክም ልጃቸው የሚያወርሱት ነገርባለመኖሩ በጣምአዘኑ ራሳቸውንሳያሻሽሉ ልጅበመውለዳቸው ተቆጩ።
ሞትአይቀርምና ከተጫናቸው እርጅናናህመ ም ምክንያትይችንአለም በደንብሳይኖሩባት ሞትአሰናበታቸው።
ከዚያም በኃላ ልጃቸው ዘመኑን የኖረው ህይወት እያሰበ ያለቅስ ጀመር።ከዚያም አልፎ ቤተሰቡን በሙሉ ማጣቱ በህመም ላይ ሌላህመም ሆነበት። ከለታት አንድቀን የሚላስ የ ሚቀመስ ባለመኖሩ ለልመና በተቀመጠ ጊዜ የታዳጊው ሁኔታ ልቡን የነካው አድሜው50ዎቹ ውስጥ የሆነ ሰው ወደርሱ ቀርቦ ሊያነጋግረው ፍቃደኛ መሆኑን ጠየቀው ልጁም በአውንታ ራሱን ነቀነቀ።
ከዚያ በኅላ ስምህ ማን ይባለል አለው። ሠፈር ውስጥ ቡቹ ነዉ የሚሉኝ። ሌላ ስም የለኝም አለ። በቀስታ እሺ ወላጆችህስ ስማቸው ማን ይባላል? እናቴ ጌጤ አባቴ ድንበሩ ይባሉ ነበር አለ በሐዘን ድምጽ። ነበር ስትል አለዉ ጎልማሳዉ መንገደኛው አይ አዉን ቤተሰብ የለኝም አለ። ህፃኑ ሰዉየዉ የራሱ ስም አክሎክ እንደ ሚባል ነግሮት ወደ ቤት ወሰደው።
ከዚያም ሲኖር ከለታት አንድ ቀን ጎህ ሲቀድ የአሳ መንጠቆ እና ብርብራ ይዞ ወደ ወንዝ ወርዶ ለፍቶ ለፍቶ አንድም አሳ ማጥመድ አቃተው። ከዚያም አረፍ ለማለት ወደ ደሴት አመራ እ ና ትንሽ ጋደም አለ ነገር ግን አንድ አጉረምራሚ ድምጽ አንተ ሰው አንተ ሰው አለው።
ዘወር ሲልም ማንም የለም። ልቡ በፍርሀት ራደ። አይዞህ አትፍራ እኔ ደሴት እባላለሁ ያረፍከው እኔ ላይ ነው አ
ከዚያም ደሴቱ አንተ እውነት ጠንካራ ነህ። በል ተነስተህ ወደ ቤትህ ሂድ። ከዚያም በረከት ታገኛለህ አለው። እሱም በማመን እና በመጠራጠር ውስጥ ሆኖ ወደ ቤቱ ያዘግም ጀመር።ቤቱ እንደደረሰም የራሱ ቤት አልመስል አለው። ብዙ የወርቅ ሳጥን፣ ውድ እቃዋች እና አልባሳት ሞልተውታል። በደስታ ዘለለ ፈጣሪውን አመሰገነ ደሴቱንም ሄዶ አመሰገነ። ከዚያም ቀን ጀምሮ ሚስት ለማግባት ወሰነ።
ከዚያም አግብቶ ወልዶ መኖር ጀመረ። ልጆቹም እሱ ባለፈበት ህይወት እንዳያልፉ ስለሚፈልግ ያሉትን ሁሉ ያደርግላቸው ነበር። ያሳዳጊውን ፈለግ በመከተል የተራቡና በልመና ያሉ ሰዎችን ሰብስቦ ሙያ ያስተምራል። ህይወቱንም ደስተኛ ሆኖ መኖር ጀመረ።

