ሁለቱ ጓደኛሞች
ሀና ተገኔ
ሀና ተገኔ

በአንድ አካባቢ የሚኖሩ በላይ እና አየለ የሚባሉ ሁለት ጓደኛሞች ነበሩ።

1

ከእለታት አንድ ቀን ሀለቱ ጎረቤታሞች ተጣሉ። እናም መግባባት አቃታቸው።

2

የሁለቱን ጓደኛሞች መጣላት ያየ ከበደ የሚባል ጎልማሳ ሰው የተጣሉበትን ምክንያት ጠየቃቸው ። በላይም ከአየለ ጋር የተጣላበት ምክንያት ሚስጥሬን ስለተናገረብኝ ነው አለ።

3

አየለም የነገረኝ ሚስጥር ስላልመሰለኝ ነው አለ። ከዛም በላይ ተናዶ መታው ሰውየውም ተገረመ።

4

መንገደኛውም ንጉስ ጋር ሄደው ችግራቸውን እንዲናገሩ ጠየቃቸው ከዛም ተስማምተው ሄዱ።

5

ንጉሱም እንዲህ ሲል ፈረደ ሁለታችሁም ላይ ጥፋት አለ። መደባደብም የለባችሁም ብሎ አስማማቸው።

6
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሁለቱ ጓደኛሞች
Author - ሀና ተገኔ
Illustration - ሀና ተገኔ
Language - Amharic
Level - First paragraphs