ታማኙ ዉሻ
ሔኖክ ጌትነት
ሔኖክ ጌትነት

ከእለታት አንድ ቀን አንድ ሰው በመንገድ ላይ ውሻ ያገኛል።

1

ከዚያም ወደ ቤቱ ይወስደው እና ምግብ ይሰጠዋል ።ከዚያም እሰውየው ቤት መኖር ጀመረ።

2

አንድ ቀን እሠውየው ቤት ሌባ ይገባል።ውሻውም ሌባ ሲገባ በመጮህ ባለቤቱን መጣራት ጀመረ ።

3

ባለቤቱም ውሻው ከእንቅልፌ ይቀሰቅሰኛል እንዴ አለና ከመኝታው ተነስቶ ደበደበው።

4

ከዚያም ሌባው መስረቁን ትቶ ወደመጣበት ተመለሠ።

5

በሌላ ቀን ይመለስ እና በሌላ ቀን ሲመጣ ውሻው እንደለመደው መጮሁን ቀጠለ ባለቤቱም ምግብ አብልቼ ፣ ከብርድ አንስቼ በተንከባከብኩህ አላስተኛ ትለኝ።

6

በማለት ሰውየው ይነሳና ይደበድበዋል። ሌባው እንደለመደው ወደ መጣበት ይመለሳል።

7

ውሻው ግን መጮሁን አላቆመም ። ወይኔ ወይኔ እንቅልፌን አጣሁ። በገዛ እጄ ተቃጠልኩ።

8

አለ እና ከመኝታው ሲነሳ ሌባውን ውሻው ነክሶት መሬት ተኝቷል። ለካ ሌባዉ እየገባ ነው።ሲጮህ የነበረው ብሎ ።

9

ሌባውን ለህግ አስረክቦ ውሻውን መንከባከብ ጀመረ።

10

ከዛም ለሌሎች ሰዎች ስለ እንስሳ ጥቅም አስተማረ።

11
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ታማኙ ዉሻ
Author - ሔኖክ ጌትነት
Illustration - ሔኖክ ጌትነት
Language - Amharic
Level - First paragraphs