ድብቁ ማንነቴ
ሚኪያስ በዳዳ
ሚኪያስ በዳዳ

በደብረብርሃን ከተማ ውስጥ የሚኖር አንድ ልጅ ነበር። ስሙም ሚኪያስ ይባላል። የሚኖረውም ከቤተሰቦቹ ጋር ነበር። ከእለታት አንድ ቀን ጓደኞቹ አብሯቸው ኳስ እንዲጫወት ጠሩት።

1

እሱም ኳስ መጫወት ይወድ ስለነበር ደስ እያለው እሺ አላቸው። አብረው እየሔዱም በመንገድ ላይ ውሀ እየተንቦራጨቁ ይሔዱ ነበር። ከዚያም ኳስ ሜዳ ደረሱ። ኳስ ሜዳው ጋር ስልክ እንጨት ነበር።

2

ከስልክ እንጨቱም ጎን ውሀ ነበር። ሚኪያስም ውሀውን አየው። እሱም ሊምቦራጨቅ አስቦ ዘሎ ውሀ ውስጥ ገብቶ ሰመጠ። ጓደኞቹም ከውሀ ውስጥ እንደምንም ብለው አወጡት።

3

ከውሀ ውስጥም ሲወጣ ልብሱ እርጥብ ሆኖ ነበር። ጓደኞቹ ኳስ ሲጫወቱ እሱ ግን ልብሱ እንዲደርቅለት ፀሀይ ላይ ቁጭ ብሎ ይመለከታቸው ነበር። ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ልብሱ ደረቀ። ወደ ቤቱም ተመለሰ።

4

እቤት ሲገባ ቤተሰቦቹ ፀጉርህና ፊትህ ምን ሆኖ ነው ነጭ የመሰለው ልብስህም ከቤት ስትወጣ ንፁህ ነበር። አሁን ግን የቆሸሸ ይመስላል ምን ሆነህ ነው? ሲሉት እሱም ፈርቶ ኳስ ስጫወት ስለነበር ነው አላቸው።

5

እነሱም ፊትህንና ፀጉርህን እንዲሁም እግርህን በሳሙና ታጠብ አሉት። እሱም እንደታዘዘው በሳሙና ታጠበ። በቀጣይ ቀን ከእንቅልፉ ሰነሳ ጉንጩ እንደ ሀዘንተኛ ሰው ተጠብሶ ነበር። ልጁም ቤተሰቡም በጣም ደነገጡ።

6

ቤተሰቦቹም ምንድነው የሆንከው እውነቱን ንገረን አሉት። እሱም በፍርሃት እውነቱን ነገራቸው። ሀኪም ቤትም ሔዶ ተመረመረና መድሀኒት ተሰጠው። ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ አልተሻለውም ፊቱና እጆቹ ላይ ጠባሳ አልነበረም።

7

ግን ሆዱ ላይ ሙሉ ለሙሉ አልተሻለውም ነበር። ይህም የሆነበት ምክንያት ለቤተሰቦቹ አደጋው ሲደርስበት ቶሎ ባለመናገሩና እውነቱን በመደበቁ ነበር።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ድብቁ ማንነቴ
Author - ሚኪያስ በዳዳ
Illustration - ሚኪያስ በዳዳ
Language - Amharic
Level - First paragraphs