

ከለታት አንድ ቀን በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖሩ ንቦች እና ሰዎችነበ። ሰዎቹም በጣም ክፉዎች ነበሩ። እነዚያ ሰዎች ንቦቹን የሚፈልጓቸው ለጥቅሞቻቸው ነበር። ማራቸውን ይወስዱባቸው ነበር። ከእለታት አንድ ቀን የንቦቹ አለቃ ሰራተኞቹን ጠራና የንቦቹን አባሎች እንዲጠሩ አዘዘ።
ከዛም ሰራተኞቹ የንጉሡን ትእዛዝ በማክበር ንጉሱ ወደ ጠራቸዉ ቦታ መጡ ።ንጉሱም እንዲህ አላቸው የሰፈሩ ሰዎች አኛን እያጠቁን ነው በጣም ክፉ ናቸው አላቸው። ለጥቅማቸው ይፈልጉናል። በማለት ምን እናድርገን አናስተምራቸው ሲል ጠየቀ። ከንቦቹ መካከል ትንሹ ንብ እንዲህ አለ። ሊያጠቁን ሲመጡ እኛም እናጥቃቸው። ብድር በምድር አይደል እንዴ አለ ትንሹ ንብ።
ሁሉም በሀሳቡ ተስማሙ። ግን ንጉሱ ንብ በሀሳቡ አልተስማማም። ንጉሱ ንብ አይ አይሆንም በማለት ተቆጣ። ንጉስ ሆይ ታዲያ ምን ይሻላል በማለት ጠየቁ። ክፉ በክፉ አይመለስም አለ።ንጉሡ ንብ ሰዎቹን ማስተማር ነው ያለብን አለ። ከዚም በንጉሱ ሀሳብ ተስማሙና ለሰራተኞቹ ሰዎቹን እንዲጠሩ አዘዛቸው።
ንጉሡ ንብ እንዲህ አለ። እኔ እዚህ የሰበሰብኳችሁ ለችግሮቻችን እንድንመካከር ነው ሲል ክፉዎቹ ሰዎች መሳቅ ጀመሩ። ንጉሡ ንብ በጣም ተናደደ በቁጣ በቃችሁ አለ።
በድንጋጤ በንጉሡ ንብ ቁጣ ደነገጡና ዝም አሉ። ንጉሡ እኛ ያጠፋነው ነገር ካለ ይቅርታ አለ። እነሱም ተነጋገሩና ይቅርታውን ተቀበሉት። ክፉዎቹ ሰዎች እኛ የራሳችንን ሐሳብ በማዳመጥ ጎድተናችኋል፤ ክፉ ስራዎችን ሰርተንባችኋልና እናንተ ይቅርታ መጠየቅ የለባችሁም፤ እኛ ግን አለብን ብለው ሁሉም ይቅርታ ጠየቁ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ንቦቹ በደስታ በመተባበር ማራቸውን መስራት ጀመሩ።

