ጥርሴ የተሰበረበት ቀን
አኪያ ካሣሁን
አኪያ ካሣሁን

ስሜ አኪያ ካሳሁን ይባላል። በደብረብረሃን ከተማ ነው የሚኖረው።

1

ከእናቴ ከአባቴ ከአጎቴ ጋር እና ከአንድ ወንድሜ ጋር ነው የምኖረው። ሁለተኛ ወንድሜን እየጠበኩ ነው።

2

እድሜዬ በዚያ ጊዜ አስር ነበር። የምማረው ጠባሴ አቡነ ጎርጎሪዮስ አጸደ ህጻናት እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነበር።

3

የአራተኛ ክፍል ተማሪ ነኝ። ብዙ የምወዳቸው ጓደኞች አሉኝ። እኔ ኳስ ጨዋታ በጣም ነው የምወደው።

4

የተወለድኩት በ2004 ነው። የአባቴ ስራ ሹፍርና ነው። የእናቴ ደግሞ የቤት እመቤት ነው።

5

ቤተሠቦቼን በጣም ነው የምወዳቸው። መምህሮቼንም በጣም ነው የምወዳቸው። አምላኬንም በጣም ነው የምወደው።

6

እናቴ ከእለታት አንድ ቀን አሟት ዋለች እናም በዚያ ጊዜ እኔ በጣም ተጨንቄ ነበር።

7

እናም በዚያን ጊዜ ማታ ላይ ለካ እናቴ ምጧ መቶ ኖራል። ከዚያን በኋላ ሊሄዱ አንቡላንስ ተጠራ።

8

እናም እናቴ ሐኪም ቤት ሄዳ ምሽት 4:00 ሰአት ላይ ወለደች።

9

ዉጪ ወጥቼ ልጫወት ስል "አይቻልም" አለች። ከዚያ "እሺ" አልኩና ተደብቄ ወጣሁ። ልጫወት ወጥቼ ዉሻ አባረረኝ። ከዉሻው ሳመልጥ ወድቄ ጥርሴ ተሰበረ።

10
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ጥርሴ የተሰበረበት ቀን
Author - አኪያ ካሣሁን
Illustration - አኪያ ካሣሁን
Language - Amharic
Level - First paragraphs