ሚስኪኑ ገበሬ
መለሰው እንግዳወርቅ
መለሰው እንግዳወርቅ

ከለታት አንድ ቀን በገጠር አካባቢ የሚናር አንድ ገበሬ ነበር።ከሰፈሩሰወች የተሻለ ገበሬ ነበር።

1

ግን ምቀኛ መጣበት አቶ ከበደ የተባሉ ሰውዮ በቅናት እህሉን ሳያይ ቆረጡበት።

2

እሱም እህሌን ማነው የቆረጠው በማለት የተሰበሰቡትን ሽማግሌወች የዘለቀን እህል ማነው የቆረጠው በማለት ጠየቁት።እኔ አላየሁም ከብት ይሆናል አለቸው።አሺ ብለው ወደ መጡበት ተመለሱ።

3

እና በሌላ ቀን ግን እህሉን ቆረጠበት።ገና ምን አይተህ በማለት ዝቶ ይሄዳል።

4

እሱም ማን ይሆን የኔ ምቀኛ እህሌን እየመጣ የሚቆርጠው በማለትለራሱ ጥያቄ የጠይቃል።

5

ከዚያ ሲመጣ ጠብቄ እይዘዋለሁ አለ"እሱም እንደ ለመደው ለቆርጥ ሲመጣ ዘለቀ ከእህሉ ወስጥ ይወጣና ይይዘዋል።

6

ከዚያም ሽማግሌወቹን ይሰበስብና እህሌን ሲቆርጥ ነው ያገኘሁት ፍርድ ስጡኝ አለቸው።አቶ ከበደ ለምንድን ነው እህሉን የምትቆርጠው በማለት ጠየቁት።

እሱም ስለበለጠኝ ቀንቼ ነው እናብትቀና አርሰህ፣ዘርተህ፣ሰርተህ ነው እንጂ መብለጥ እሱ የለፋበትን ለምን ትቆርጣለህ በማለት መከሩት።

7

እሱም ዘለቀ ይቅር በለኝ የዘራሀውን ቆረጥኩብህ በማለት ተፀፅቶ ጠየቀው።እሱም ይቅርታውን ተቀብሎ ተስማምተውመኖር ጀመሩ።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሚስኪኑ ገበሬ
Author - መለሰው እንግዳወርቅ
Illustration - መለሰው እንግዳወርቅ
Language - Amharic
Level - First paragraphs