አዲሱ ልብሴ
እጹብ አብዱ
እጹብ አብዱ

ሀና እባላለሁ ቀኑ ለባእል 5ቀን ሲቀረዉ ነበር። እናቴ ወደ ልብስ ቤት ወስዳኝ በጣም የሚያምር ቀሚስ ገዛችልኝ ቀለሙ ቀይ ፣ነጭ ነጠብጣብ ያለበት ቆንጆ ቀሚስ ነው።ማውለቅ አልፈለኩም።

1

እንደ ገባሁ ለጓደኞቼ አሳየዃቸው እነሱም ወደውታል።ፋሲካ ደርሶ ለመልበስ ቸኩያለሁ ማንም ሳያየኝ አደርኩ ጠዋት ስነሳ ሁሉም ሳቁብኝ እንደዚህ እንደዚህ እያለ ቀኑ ሄደ የበአሉ ቀን ደረሰ።

2

ተጣጥቤ ለበስኩት በጣም ደስ አለኝ።ምግቡ ሽታው ይጣራል
። ድንገት ወደ እናቴ ጋር ስሮጥ ወጡን ደፍቸው ቀሚሴ ተበላሸ በዛን ሰዓት ያሰብኩት ስለ ቀሚሴ ብቻ ነበር ወጡ ትዝ አላለኝም ደንግጬ ጮሁኩኝ።

3

ታናሽ እህቴ ከእንቅልፏ ነቅታ መጣች ወዲያውኑ እናቴ ደንግጣ መጣች ተቆጣችና እህቴን ስታያት ከፍቷት ነበር ምክንያቱም ለሷ ቀሚስ ስላልተገዛላት ነዉ።እናቴ"ፍቅርዬ ምነው " አለቻት መልስ ሳሰጣት ሄደች በሩ ሲንኳኳ ረሳናት።

4

ደስ ሲል አጎቴን አክስቴና ልጆቹ ናቸው የመጡት ሰላም አሉንና "እንዴ ፍቅርስ የት ሄደች" ውይ ፍቅርዬ ረሳኋት የኔነገር ፍቅር ፍቅር ብላ ተጣራች "ይዣት ልምጣ" አልኩ።

5

"ፍቅርዬ አጎቴ መቷል እኮ"እምቢ አልመጣም ልብስ ግዙልኝ"ባለፈው አይደል የተገዛልሽ "አጎቴ መጣና አናገራትና ተያይዘው ወጡ።

6

"ነገ ወደ ልብስ ቤት ሄደን እንገዛለን"በነገታው ተገዛላት።አገናዛቢ ልጅ ሆነች ።በዓልንም በጥሩ አሳለፍን ።

7
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አዲሱ ልብሴ
Author - እጹብ አብዱ
Illustration - እጹብ አብዱ
Language - Amharic
Level - First paragraphs