ኤሊ እና ተንኮሉ
በላይ አብነው
በላይ አብነው

ከእለታት አንድ ቀን ወፎች ሁሉ ወደ ሠማይ ቤት ለግብዣ ተጠሩ። በዚህ የተነሣ ሁሉም ተደሠቱ። ለዚህ ታላቁ የግብዣ ቀን ዝግጅት ማድረግ ጀመሩ። ይህም ማለት ላባቸውን በተለያዩ ቀለማት ማስዋብ ማለት ነው። ታዲያ በዚያው በወፎች መንደር አከባቢና ናሎ የሚባል ከሚስቱ ጋር የሚኖር አንድ ተንኮለኛ ኤሊ ነበር።

1

በአንድ ማለዳ ወፎች ሁሉ ባሉበት ከነሱ ጋር ወደ ሰማይ ቤት ለግብዣ መሄድ እንደሚፈልግ ነገራቸው። ወፎች
ግን አንተ አታላይ መሆንህን ስለምናውቅ ከእኛ ጋር እንድትሄድ አንፈቅድም አሉት። እሱ ግን እኔ በጣም ተለውጫለሁ በማለት ነገራቸው።

2

ስለዚህ መለወጤን ተረድቻለሁ ዉሰዱኝ በማለት በጣፋጭ አንደበቱ ሠባብኮ አሳመናቸው። ከዚህ በኋላ ሁሉም አንድ ለባ አዋጡለት። ሁለት ክንፎች ተሠሩለት። በዚህን ጊዜ ሲታይ ከቀሩት ወፎች ላባ ተነቅሎ በልዩ ዲዛይን ተሰተካክሎ የተገጣጠመ ስለሆነ ቀለሙ ህብር አስደናቂ ግርማ ሞገስ የሚያሰጥ ሆነ።

3

ላባቸውን በያይነቱ አምጥተው ጠረጴዛው ላይ ቆለሉለት። በዚህን ጊዜ ኤሊ ሆዬ ብድግ አለና ስለተደረገላቸው ግብዣ በጥሩ ቃል ምስጋናውን አቀረበ። ስለዚህ ይህም ግብዣ የመጣው ለኔ ነው እናንተ ተራችሁን ጠብቁ አላቸው። ብለው በማሠብ ዝም ብለው ያዩታል። አጅሬው ኤሊም ምግቡንና መጡን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ ወፎቹም ሌላ ምግብ ይመጣል ቢጠብቁ አላገኙም። ወፎች እንዳታለላቸው ገባቸው።

4
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ኤሊ እና ተንኮሉ
Author - በላይ አብነው
Illustration - በላይ አብነው
Language - Amharic
Level - First paragraphs