ጅል ባል እና ሚስት
ሜሮን ሀይለኛው
ሜሮን ሀይለኛው

በገጠሩ የሀገራችን ክፍል የሚኖሩ ሁለት ባል እና ሚስት ነበሩ እኝህ ባል እና ሚስት ጥቁር በሬ አላቸው

1

ከእለታት ባንዱ ቀን ሚስት ለባሏ ስጋ አማረኝ አለችው እሱም አንቺ ከአማረሽ በሬውን አርደን እንበላዋለን አለ

2

በሬውን አርደው እንዲበስል በገንቦ ጣዱት ።ለጥርሳቸው መጎርጎሪያ ሊያመጡ ቤቱን ሳይዘጉ ወጡ

3

በመንገድ ላይ ሁለት ሰዎች አገኙና ፡እዛ ጭስ የሚወጣበት ቤት ውስጥ ስጋ ጥደናል እንዳትበሉብን ብለው ሄዱ ።ሰወቹግን ገብተው ስጋውንበልተው አጥንቱን አስቀርተው ሄዱ

4

እነሱም ጓሳ ይዘው ከመጡ ቡሀላ ገንቦውን ሲመለከቱ ባዶ ነበረ።ከገንቦው በላይ ዝንብ አዩና የበሉብን ዝንቦቹ ናቸው ማለት ነው ባል ፥ፍርድቤት ሄጄ እከሳለሁ አለ

5

ፍርድቤት ሄዶ ለዳኛው ፦ልንበላ የጣድነውን ሰጋ በልተው ጠበቁን ፍርድ ይሰጠን አለ

6

ዳኛው ያሉትን ሰማና እንደሱማ ከሆነ ዝንቦቹን አናት አናታቸውን በሏቸው አለ

7

ባልም ሚስቱ ጋርሄዶ ዳኛውኮ ዝንቦቹን አናት አናታቸውን በሏቸው ብሏል አለኝ አላት እሷም ጎሽ ትክክለኛ ፍርድ ነው በል እንበላቸው አለች

8

ዝንቦቹን ሲመቱ ከቆዩቡሀላ ሚስት ደክሟት አረፍ እንዳለች አንዷ ዝንብ አፍንጫዋ ላይ አረፈች ባሏን በእጇ ጠርታው በላት አለችው እሱም ዝንቧን ስቶ ሚስቲን ገደላት

9

የቀብሯ እለት ምን ሆና ነው ሲሉት እንጃ እንደው ስቃ ቀረች አለ

10
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ጅል ባል እና ሚስት
Author - ሜሮን ሀይለኛው
Illustration - ሜሮን ሀይለኛው
Language - Amharic
Level - First paragraphs